‹‹የአላህን ነቢያትና መልክተኞቹን በተመለከተ ከተላለፉት የተዛቡና ተአማኒነት ከጎደላቸው ዘገባዎች መካከል መስከራቸውን፣ወይም ዝሙት ላይ መውደቃቸውን፣ወይም ሰዎች እንዲገደሉ ትእዛዝ መስጠታቸውን . . የሚያወሩ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ በአላህ ለተመረጡ ምርጦችና የሰው ልጆች ፈርጦች ከሆኑ የአላህ ነቢያት ቀርቶ በመልካም ስነምግባር ለታነጸ ተራ ሰው እንኳ የማይገባ መሰረት የለሽ ተረት ነው። ከመሰል ተረቶች መካከል ነቢዩ ዳውድን አስመልክቶ (ሳሙኤል ካልዕ 11፣2-26)፤ስለ ኢያሱ ወልደ ነወዌ የቀረበው (ኢያሱ 6፣24)፤ነቢዩ ሙሳን አስመልክቶ የሰፈረው (ዘኁልቁ 31፣14-18) እና ሌሎቹም መሰል ጥቅሶች ለአላህ ክቡራን ነቢያት ፈጽሞ የማይገቡ ናቸው።››