እምነትና የስነልቦና ጤንነት

እምነትና የስነልቦና ጤንነት
‹‹ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ውስጥ የከሰለጠነው ዓለም ሕዝቦች የተለያዩ ግለሰቦች የምክር አገልግሎት ሰጥቻለሁ።በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን አክሜያለሁ። በመካከለኛው የዕድሜ ክልል ማለትም ሰላሳ አምስት ዓመት ከሆናቸው መካከል የችግሩ መንሥኤና የሕመሙ መነሻ ኢአማኝነትና በሃይማኖት ትምህርቶች ላይ ማመጽ ያልሆነ አንድም አልገጠመኝም። እያንዳንዱ ታማሚ የበሽታው ሰለባ የሆነው ሃይማኖት የሚያስገኘውን የመንፈስ እርካታና ውስጣዊ መረጋጋት የተነፈገ በመሆኑ ነው ማለት ይቻላል። ከነዚህ መካከል ወደ እምነቱ ተመልሶ ሕይወትን ለመጋፈጥ በሃይማኖት ትእዛዛትና እገዳዎች ሳይታገዝ የተፈወሰ አንድም ሰው አልነበረም።


Tags: