‹‹ከሙሐመድ በፊት የነበሩ ነቢያት ተአምራት በእርግጥ ጊዜያዊ ነበሩ። ቁርኣንን ግን ተጽእኖ ፈጣሪነቱ ቋሚና ቀጣይ በመሆኑ ‹‹ዘላለማዊው ተአምር›› ብለን ልንሰይመው እንችላለን። አንድ አማኝ በየትኛውም ጊዜና ስፍራ የአላህን መጽሐፍ በማንበብ ብቻ ይህን ተአምር በቀላሉ ማየት ይችላል። በዚህ ተአምር ውስጥም እስላም ላስመዘገበው ሰፊና ፈጣን የስርጭት ሽፋን አሳማኝ ምክንያትና ትንተና እናገኛለን። አውሮፓውያን ቁርኣንን ስለማያውቁት ወይም ተአማኒነት የሚጎድላቸው ብቻ ሳይሆኑ ሕይወት አልባ በሆኑ ትርጉሞች አማካይነት ብቻ የሚያውቁት በመሆኑ የዚህን ፈጣንና ሰፊ ስርጭት መንስኤ ምን እንደሆነ አይረዱም።››