-ጆርጅ . . ጆርጅ፣ካለህበት ነገር መገላገል አትፈልግም?
-ምን ማለት ፈልገሽ ነው?! አዎና እፈንዴታ!
-አዲሷ ጎረቤታችን ቶም አሪክሰን የተባለ ታዋቂ የስነ ልቡና ሐኪም መኖሩንና እርሱ ዘንድ መታከሟን አንስታልኝ ነበር።
-መልካም . . ወደ ስነ ልቦና ሐኪም የምሔደው እባክህን ለምን እንደ ተፈጠርኩና ለምንስ እንደምኖር የማላውቅ መሆኔን እንዴት እንምረሳ አስተምረኝ ብዬ ልጠይቀው ነው?
-ሳይሆን ለምን እንደ ተፈጠርኩና ለምንስ እንደምኖር እንዴት ማወቅ እችላለሁ ብለህ ልትጠይቀው ነው።
-ምላሹን ላውቀው !!
-አዎ።
-ጆርጅ! አለች፡፡
-አዎ . . አዎ . . ሐኪሙ ዶክተር ቶም ፕሮትስታንት ነው? ወይስ እንዲህ መጓጓትሽ በሌላ ምክንያት ነው? ብዬ ልጠይቅሽ ነበር።
-ጆርጅ የኔ ፍቅር . . ጉጉቴ ደስተኞች ሆነን አብሬን እንድንኖር ነው፣እኔ ከገዛ ራሴ ሆን ብዬ የምሸሽ መሆኔን በሚመለከት ምናልባት ትክክለኛ ልትሆን ትችላለህ፣ግና አንተ ከምትመራው የመደናገርና የጥርጣሬ ሕይወት የተሻለ አይመስልህም ?!
-መልካም፣የደስተኝነትን መንገድ ፈልጌ ለማግኘት ወስኛለሁ፣ ከዛሬ ጀምሮ መልስ ለማግኘት ጥረት አደርጋለሁ እንጂ ከራሴ አልሸሽም . . ፈገግ አለና ቀጠለ ፡- ነገር ግን መንገዱን ከካቶሊክ ቄስ ዘንድ ለማግኘት ፍለጋ አልሄድም፣ቆይኝማ መጀመሪያ ስለዚህ ሐኪም ልጠይቅ።
-አጠያይቀን እንፈልገዋለን፣ፈውስህን በርሱ እጅ ያደርግ ዘንድ ለጌታ እጸልያለሁ።
-አሃ፣እናም እኔ ሕክምና የሚያስፈልገው ሕመምተኛ እንጂ ለጥያቄው ምላሽ የሚያፈላልግ ፈላስፋ አይደለሁም ማለት ነዋ !
-መታከሙ ራሱ ወደ ምላሹ ለመድረስ እንጂ ታማሚ ስለሆንክ አይደለም . . በዐይኗ ጠቀስ አድርጋ ደረቱ ላይ በመለጠፍ ፡- ተስማማን የኔ ፍቅር? አለች።
-ተስማምተናል !
የማያስደስቱ ግለሰብ ብቻ ነበር፡፡ ጆርጅ ቀጠሮ እንዳለው ሲነግረው፣በጣም ቀዝቀዝ ባለ ሁኔታ ፡-
-ስሜ በራድ ነው፣ከዚህ በፊት አይቼህ አላውቅም፣ዶክተሩ አሁን ሥራ ያላቸው ይስለኛል፣ አለው።
-ቀጠሮ አልያዝሽልንም ነበር? አላት።
-ይዣለሁ እንጂ ! ከሦስት ቀናት በፊት መጥቼ ነው ቀጠሮ የተቀበልኩት፡፡
-አዎ . . አዎ . . ይቅርታ ቀጠሮ ወስደሻል፣ኑ ግቡ እየጠበቋችሁ ነው፡፡
-ግን እኮ ቀጠሮው ለኔ ብቻ ነው የተያዘው !
-ካትሪና ባለቤትህ ነች፣ ከሁሉም ይበልጥ ቅርብህ ናት፣ ሁኔታህን ለመረዳት ብዙ ልትጠቅመኝ ትችላለችና በቅድሚያ ከርሷ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ተነጋግሬ ከዚያ ካንተ ጋር እቀመጣለሁ፡፡
-ቶም ከካትሪና ጋር ነዋ !
-ስሟን እንዴ ማወቅ ቻልክ ?
-ከሦስት ቀናት በፊት የመጣችው እሷ አልነበረችም . . አለና በምጸት ፈገግ አለ። ቶም ለብቻው ከርሷ ጋር ይቀመጣል፣ዶክተር ቶም መቼም በጣም እድለኛ ነው፣ መልከ መልካም ሎጋ ወንድ የምሥራቅ መስህብነት ካላት ውብ ሴት ጋር . .
-የኔ ፍቅር ዶክተሩ አንተን እየጠበቀ ነው፣አሁን ቤተክርስቲያን ቀጠሮ ስላለብኝ እኔ መሄድ አለብኝ።
-ማን እንደ ፈጠረህ፣ለምን ዓለማ እንደምትኖርና መጨረሻህ ምን እንደሚሆን ማወቅ የምትፈልገው ለምንድነው? አለው።
-መንፈሴና ሕይወቴ ተቀናጅተው ዓላማና ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖረኝ ስለምፈልግ ነው።
-አሀ፣ ልዩና የብሩህ አእምሮ ባለቤት የሆነ ምሁር ሁኔታ ያጋጠመኝ መሰለኝ፤ለምን የፍልስፍናዊ አስተሳሰብ መንገዶችን አትጠቀምም?
-ማለት የፈለከው ነገር አልገባኝም?
-አንተ ፈላስፋ እንዴት ነው ያልተረዳኸው! በፍልስፍናዊ መንገድ መልስ ስንሰጥ እያንዳንዱ መልስ ምላሽ ለመስጠት በሚያግዙ ጥቅል ጥያቄዎች ላይ የሚሞረከዝ ይሆናል።
-ለጥያቄዎችህ ምላሽ ለማግኘት ሌሎች ጥያቄዎችን አቀርብልሃለሁ። ለምሳሌ ፡- መልሱን ከዬት ማግኘት እንችላለን? ወደ ምላሹ ተልቀን ከመግባት ፈንታ ከየት ልናገኘው እንችላለን? ትክክለኛ ስለመሆናቸው መለኪያቸው ምንድነው? የሚለውን እንመልከት። ይኸኛው ምክንያታዊና ፍልስፍናዊ የሆነ አርኪ መንገድ አይመስልህም?
-ምናልባት !
-ምላሹን ከውስጥህና ከመንፈስህ ውስጥ ለማስወጣት ይህ መንገድ በጣም ምርጥ ነው። ፈገግ ብሎ ቀጠለና ፡- እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ነገሮችን አእምሮን ሳይጠቀሙ እንዳው አምኖ በመቀበል ላይ ከተመሰረተው የካቶሊክ መንገድም ያለ ጥርጥር የተሻለ ነው! ቀጠሯችን መጪው ሳምንት ነው። ቀጥሎ ላሉት ሁለት ጥያቄዎች መልስ ይዘህልኝ ለመምጣት ሞክር። ወደ መልሱ መድረስ የምንችለው በየት በኩል ነው? ለምላሹ ትክክለኛ መሆንና አለመሆን ዋስትናው ምንድነው? ተስማማን?
-ስለ ካቶሊካዊነት የተናገርከው መጥፎ ከመሆኑም ጋር ሎጂካዊና ምክንያታዊ ነውና ተስማምተናል።
-መልካም የሕክምና ጉብኝት፣ ሰላምታዬን ለካትሪና አድርስልኝ !
-ቡናውን አቅርበህ ማስቀመጥህን ጭራሽ አላወቅኩም ብልህ ታምናለህ፤ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊ ጥያቄዎቻችን የገዛ ራሳችንንም እንድንረሳ ያደርጉናል !
-ውስጣዊ ጥያቄዎች የንቁነትና የብልህነት ምልክት ናቸው፤ ይሁን እንጂ . . ሲበዙ ግን ውስጣዊ ትግል፣ የሃሳቦችና የእምነቶች የርስበርስ ፍጭት መኖሩን የሚጠቁም ምልክት ይሆናሉ።
-ባንተ ግምት የነዚህ ፍጭቶች ወይም ቅራኔዎች ምክንያት ምንድነው?
-ምክንያቶቹ በርካታ ናቸው፤ከዋነኞቹ መካከል፣ ለምንድነው የተፈጠርነው? የምንኖርለት ዓላማ ምንድነው? መጨረሻችንና መመለሻችንስ ወዴት ነው? የሚሉትን የመሳሰሉ ታላላቅ የሕይወት ጉዳዮችን በተመለከተ ባለቤቱ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ገና ያልደረሰ መሆኑ አንዱ ነው። ችግሩ ያለው ነገሮችን ውስብስብ በማድረጉ ላይ ነው። ነገሮችን ቀለል አድርጎ መውሰድ ለጥያቄዎቹ፣ በአብዛኛው ከአፍአዊነት የማያልፈው ውስብስብነት የማይሰጠንን ጥልቀት ያለው ምላሽ ይሰጣናል!
-ለነዚህ ጥያቄዎች እንዴት ነው በቀላሉ ምላሽ ማግኘት የምንችለው?
-ብዙዎች በአልባሌ ነገር፣በመጠጥ፣ወይም በወሲብና በሌሎች ነገሮች ውስጥ ከምላሹ ይሸሸጋሉ። ጥያቄው በራሱ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የሕሊና ንቃት ምልክቶች አንዱ ነው፤ግና . .
-ጌታዬ ማንን ማለትዎ ይሆን?
-ከግማሽ ሰዓት በፊት መጥጬ ያስተናገደኝ ሌላ ሰው ነበር።
-ምናልበት ካት ወይም አደም ይሆናል፤ተራቸው ከአንድ ሰዓት በፊት አብቅቶ አሁን የኛ ተራ ነው።
-የካት ወይም የአዳም ተራ መቼ ነው የሚጀምረው?
-ነገ ጧት ከሦስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አስራ አንድ ወይም አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ ነው።
-አመሰግናለሁ።
-የዶክተሩ ነገር እንዴት ሆነ ?
-በመጠኑ አሳማኝ ቢሆንም እንግዳ ባሕርያት ያሉት ሐኪም ነው። ከዚያም ወደ ካትሪና ፊቱን አዞረና ጠበቅ ባለ አነጋገር ፡- ለብቻችሁ በተቀመጣችሁ ጊዜ ካንቺ ምን የፈልግ ነበር?
-የኔ ፍቅር አላውቅም፤ተቀበለኝና ራሱን አስተዋውቆ ችሎታውን ነገረኝ፤ከዚያም ስለ ሥራዬና ስለ ኑሮዬ ጠየቀኝ . . ስልጡንና በጣም የተገራ ሰው ነው።
-መልከ መልካም ሎጋም ነው! ስለኔ ምንም አልጠየቀሽም?
-ልወጣ ስል ጠይቆኝ የሕይወትን ምንነት የሚመለከቱ ጥያቄዎችህ እንደሚያስጨንቁህ ነገርኩት።
-ይኸው ብቻ ነው ? !
-ይኸው ብቻ ነው፤አብዛኛውን ጊዜ ስለራሱና ስለኔ ነበር የሚናገረው። እንዴት ያለ ጨዋ መሰለህ!
-አይ፣በሃይማኖቶች የማያምንና ሃይማኖተኝነትን የሚዋጋ፣ ሃይኖማቶችን በሽታ አድርጎ የሚመለከት ኤቲስት ከመሆኑ ጋር፣ስለርሱ የምትናገሪው የሚገርም ነው። እንደሚመስለኝ ጋጠ ወት ባለጌም ነው !
-ጆርጅ ! ከኔ ጋር እጅግ በጣም ጨዋና ትሁት ነበር! የስነ መለኮት መምህርት መሆኔን ካወቀ በኋላ እንኳ ስለ ሃይማኖት በጭራሽ አላነሳልኝም። ለማንኛውም አንተ ወደርሱ የሄድከው ለሚሰጠው ሕክምና እንጂ ለሃይማኖቱም ሆነ ለስነ ምግባሩ ብለህ አይደለም !
-ያመሸሽውና ስትጠጭ የነበረው ከማን ጋር ነው?!
-ተቆጣጣሪዬ አይደለህም፤መልስ አለመስጠት መብቴ ቢሆንም ለማንኛውም በቄሱ ቡራኬ ሰጭነት በተመራ ድግስ ላይ ነበርን።
-የጥያቄዎች ስብስብ ነበረኝ፣እርሱም በጥያቄዎቼ ላይ ጥያቄ በመደናገሬ ላይ ሌላ መደናገር ነው የጨመረልኝ !
-እንዴት !
-ለጥያቄዎቼ መልስ እንደመስጠት ሌሎች ጥያቄዎችን ጠይቆኝ መልስ እንድሰጥባቸው ጠየቀኝ።
-ሌሎች ጥያቄዎችሌሎች ጥያቄዎች !
-አዎ፣ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የምናገኘው ከየት ነው? መልሶቹ ትክክል ስለመሆናቸው ዋስትው ምንድነው? የሚሉ ናቸው።
-ጥያቄዎቹ እንግዳ ከመሆናቸውም ጋር ምናልባት እውነቱን ሊሆን ይችላል !
-ይህን እርሽው፣ ዛሬ እውስጤ ጠልቆ ስሜትን ከነካ ሌላ አስደናቂና ሰው ጋር ተገናኝ፣ሐኪሙ ዘንድ በሄድኩበት ያው ጉዳይ ላይ ባልጠበኩት አጋጣሚ አነጋገረኝ!
-በዚያው ርእስ ላይ!
-ይህ መቼም እጅግ የሚገርም አጋጣሚ ነው!
-ምን አለህ ?!
-በትክክል ይህ ነው ማለት አልችልም፣ከኔ ጋር የጀመረውን ውይይት አልቋጨውም። ይሁን አንጂ ከቶም በተቃራኒ ሃይማኖተኛ ሰው ይመስለኛል። ጥያቄዎቹን ውስብስብነት በሌላው ቀለል በሆነ ሁኔታ ስለመመለስ፣ቀለል ማድረግ ጥልቀት ያለው ስለመሆኑ፣ስለ ሕይወት ትርጉምና ስለ ደስተኝነት ይናገር ነበር። ዓይኖቿን ትኩር ብሎ እየተመለከተ ፡- ሰዎች ከምላሹ በመሸሽ አስካሪ መጠጥ በመጠጣት፣ በማምሸት፣በመጨፈርና በመሳሰሉት ውስጥ ራሳቸውን ከራሳቸው ለመሸሸግ የሚሞክሩ ስለ መሆናቸውም ሲናገር ነበር !
-ሃይማኖተኛ በመሆኑ ንግግሩ መልካም ሲሆን፣ሰዎች ከምላሽ መሸሻቸውን በተመለከተ ግን ምናልባት ትንሽ ያከረረ ሳይሆን አልቀረም ! ‹‹አፈገገችና›› ፡- ምናልባት ካቶሊካዊ ይሆናላ ! የኔ ፍቅር ምናልባት ስለደካከመህ በምትናገረው ጉዳይ ላይ ትኩረትህን መሰብሰብ አልቻልክም !
-ምናልባት . . አዎ ምናልባት፣ለማንኛውም ግን ውስጣዊ ስሜቴን ነው በጥልቀት የቀሰቀሰው፡፡ አሁን እንተኛ፣ነገ ብዙ ሥራ አለብኝ።
-ቀጠሮአችን ረቡዕ ምሽት ሁለት ሰዓት ነው፤ቤተክርስቲያኑ ውስጥ አብረን እናመሻለን።
-ማነው የደወለው?!
-ካቶሊካዊነትን መማር የሚፈልግ ሰው ነው።
-በምሽት ድግስ ነው የሚማረው !
-ቤተክርስቲያን ውስት የሚደረግ የምሽት ድግስ እንጂ የመሸታ ቤት የብልግና ጭፈራ አይደለም! በመካነ መቃቢር እንዲማር ትፈልግ ኖሯል ! ተወንና አሁን እንተኛበት፣ በጣም ስሱ ሆነሃል።
-ሠላም ደህና አደርክ።
-ሠላም ደህና ነኝ።
-የትናንቱ የሐኪም ቤት ውሎህ እንዴት ነበር?
-ምንም አይልም፤ገና በጅምር ላይ ስለሆነ አድሮ ውጤቱ ወደፊት ይታወቃል።
-መልካም፣ግና ጊዜህንና ገንዘብህን ነው የምታባክነው፤ስለነዚህ ጉዳዮች ማሰብና መጨነቅ ጊዜን ማቃጠል ነው። ለኔማ የበለጠ የሚከፍለኝን ሰው ብትነግረኝ ከፈለክ አምላኬ አድርገዋለሁ . . ክተክት ብሎ ሳቀና ፡- ትናንት የመጣ አስቸኳይ ሥራ ስላለን ወደቢሮዬ ብትመጣ ትሩ ነው፣ አለው።
-ጥሩ፣እመጣለሁ ከተቻለ ግን ካንድ ሰዓት በኋላ ነው።
-መልካም፣ ካንድ ሰዓት በኋላ።
-ወዳጄ፣ሐኪሙ የሚወሰውስህን አከመህ ወይ? ተፈወስክ ?
-እኔ የተወሰወስኩ አይደለሁም፤አልታመምኩምም። ወደ ዶክተሩ የሄድኩት ለጥያቄዎቼ መልስ እንዳገኝ ይረዳኝ ዘንድ ነው።
-ነገሩ ላንተ የምር ይመስላል፤ላጫውትህ መቀለዴ ነው፤የኔን አቋም በሚገባ ነው የምታውቀው፤ጉዳዩን እርሳውና ሀብትህን ለመጨመር በኑሮህ ለመደሰትና ሕይወትን ለመቅጨት ትጋ . . ወደ ዋናው ጉዳይ እንመለስና ካንተ ጋር ለመገናኘት የፈለኩት ሕንድ የሚገኘው የሠራተኛ አስቀጣሪ ኩባንያ የኛን መመዘኛዎች መቀበሉን ሳለ አሳወቀን ነው። እኛም ከነሱ ዘንድ ብዛት ያላቸውን ሠራተኞች በአስቸኳይ መቅጠር ያስፈልገናል። እዚያው ሕንድ አገር ከሚገኘው የሶፍትዌር አከፋፋይ ኩባንያ ጋርም ትብብራችንን ማጠናከር እንፈልጋለ። ስለሆነም በሁለት ሳምንታት ውስጥ አንዳችን ወደ ሕንድ መጓዝ የግድ ሆኗልና አንተ ዝግጁ ነህ ወይ?
-በዚህ ጥድፊያ?!
-ከይቅርታ ጋር አዎ፤እንደምታውቀው የባለ ንብረቶች ቦርድ ስበሰባ ከሁለት ሳምንት በኋላ በመሆኑ እኔ መሄድ አልችልም።
-የራሴን ሁኔታዎች አይና ከሰሞኑ ስለጉዞዬ አሳውቀሃለሁ። የውሎቹንና የስምምነቶቹን የተሟላ ቅጂ በውስጥ መረብ ላይ አድርግልኝና አንብቤ ልመርምራቸው። ነገሮች ግልጽ ከሆኑልኝ በኋላ በመጪው ሳምንት እንገናኝ።
-እናም ቀጠሯችን መጪው ሳምንት ነው። ራስህን ለጉዞው ዝግጁ እንድታደርግ ምኞቴ ነው . . መሰሪ ፈገግታ አሳየና ሐኪሙን ወዲያ በለውና መጪው ሳምንት የሚነገርህ ድንገተኛ የምስራች እኔ ዘንድ ታገኛለህ።
-ጌታዬ ምን ልታዘዝ?
-መልካም ፈቃድህ ከሆነ ቡና . . ይቅርታ አንዴ . . ስምህ ካት ነው ወይስ አደም?
-ጌታዬ አደም ነኝ።
-አብረን እንድንጫወት መቀመጥ ትችላለህ?
-ጌታው ይቅርታ፣እርስዎን ማገልገል ደስ ባለኝ ነበር፤ግና መፈጸም የሚገባኝ የሥራ ኃላፊነት አለብኝ።
-የሥራ ሰዓትህ ሲያበቃ በመኪና እንዳደርስህ ትፈቅድልኛለህ?
-ይህ የርስዎ ደግነት ነው፤እኔ ፈቃደኛ ነኝ . . ቢያንስ አውቶብስ አልሳፈረም ማለት ነው . . ተራዬ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ያበቃል።
-እስከዚያ ቡናዬን እጠጣለሁ፤አንተን ለማድረስ ደስተኛ ስለመሆኔ እርግጠኛ ሁን።
-አመሰግናለሁ፤ይፍቀዱልኝ።
-ተዘጋጅቻለሁ፣እንሂድ? አለው።
-እኔም ዝግጁ ነኝ፣ወደ ቤትህ መሄድ ትፈልጋለህ? ወይስ እዚህ ካፌ ፍንጃን ቡና? ወይስ በቅርበት በሚገኝ ሬስቶራንት እራት ልጋብዝህ?
-ምርጫው የኔ ከሆነ፣ሦስተኛውን ነው የምመርጠው።
-እዚህ ቅርብ ያለው የደስተኝነት ሬስቶራንት አመቺ ሊሆን ይችላል።
-በጣም አመቺ ነው፣ስሙ ይማርከኛል። ደስተኝነት በግራ መጋባት፣በጥርጣሬና በዕድለ ቢስነት ዘመን፣በአሳዛኝ መልኩ ብዙዎች የተነፈጉት ውብ መንፈስ ነው!
የአዳም ቃላት ጥልቅ ስሜቱን የነኩት፣ውስጡን የኮረኮሩትና የከበቡት መሆናቸው ቢሰማውም ጆርጅ ግን ዝምታን ነው የመረጠው።
-በል የምትፈልገውን እዘዝ፣ አለው።
-የዓሳ ጥብስ ከአረንጓዴ ሰላጣ ጋር ይሁንልኝ።
-ለኔ የበሬ እስቲክ ከድንች ጋር አምጣልኝ።
-እነሆማ አንተ እንደምትለው፣በግራ መጋባት፣ በጥርጣሬና በዕድለ ቢስነት ዘመን . . ብዙዎች በተነፈጉት የደስተኝነት ምግብ ቤት ውስጥ ነን፣ አለው።
-እህ፣አዎ፤ጥርጣሬና ግራ መጋባት ሕይወትን ትርጉም ስለሚያሳጡ፣ ሰዎች ወደ ግዑዝ እቃነት፣ እንቅስቃሴው ትርጉምም ሆነ ጣዕም ወደ ሌለው፣ ደስተኝነትና ተድላን መኖር ቀርቶ ማወቅ እንኳ ወደማይችል መገልገያ ቁሳቁስነት ይለወጣሉ።
-እናም አንተ ከግራ መጋባትና ከጥርጣሬ ወደ ጭፍን አምኖ መቀበል መሸሽን ከሚደግፉ ወገኖች ነህ ማለት ነው።
-ፈጽሞ . . ፈጽሞ፣ ያልሆነውን መስሎ ለመታየት ቢሞክር እንኳ ሽሽት የባለቤቱን ሁኔታ ይበልጥ የከፋ ያደርጋል። የመጀመሪያው ራበኝ ብሎ የሚጮህ ረሃብተኛ ሲሆን፣ ሁለተኛው ለመተኛት የሚጮህ ረሃብተኛ ነው !
-አሃ፣እናም ሁለቱም የተራቡ ናቸው !
-ሆኖም የመጀመሪያው የገዛ ራሱን ነፍስ አያያዝ በተመለከተ ከሁለተኛው የበለጠ አእምሮና ብልህነት አለው።
-በእውነተኝነት መልስ ስጠኝማ። አንተ ደስተኛ ነህ ወይ?
-ቀላል መልስ ትፈልጋለህ ፡- አዎ፣ደስተኝነት ማለት እኛ ራሳችን ስለራሳችን፣ስለ ሕይወትና ስለ ፍጥረተ ዓለም የሚኖረን አመለካከት ውስጣዊ ስሜትና ግንዛቤ ነው።
-ያንተ ደስተኝነት እንደ አንተው ሃይማኖተኛ የሆነችው ባለቤቴ ደስተኝነት - ባንተ አባባል መልሶቹን ላለመፈለግ በመጠጥና በምሽት ጭፈራ ውስጥ ራስን መደብቅ ! - እንዳይሆን እሰጋለሁ። ከአጭር ዝምታ በኋላ ፡- ባንተ አመለካከት የሕይወት ትርጉም ምንድነው? ሲል አስከተለ።
-ለታላቆቹ ጥያቄዎች ምላሽ መፈለግን የሚሸሽ ሰው፣ አስመስሎ ቢተውን እንኳ የደስተኝነት ስሜት ሊኖረውና ደስተኛ መሆን አይችልም። የሕይወት ትርጉምን የሚመለከተው ጥያቄህ፣ለምን ዐላማ ተፈጠርን? ለምንስ እንኖራለን? መጨረሻችንስ ወዴት ነው? የሚሉ የሦስቱ ጥያቄዎች ሌላ ቅንብር ነው።
-የሦስቱ ጥያቄዎች መልስ ምንድነው?
-የደስተኝነት ስሜት የሚሰማው፣ጣዕሙን የሚየውቅና መዓዛውን የሚያሸት ሆኖ የነዚህን ጥያቄዎች ምላሽ የማያውቅ ሰው ይኖራል ብለህ ታምናለህ ?!
-በግልጽ መልስልኝ፣የነዚህን ጥያቄዎች መልስ ታውቀለህ ወይ?
-ለኔ በጣም ግልጽና አሳማኝ የሆኑ መልሶች አሉኝ ብዬ ነው የማምነው። ነገር ግን መልስ ማለት አራሴን አመለካከት ባንተ ላይ ማንቆርቆር ማለት አይደለም። እንደሚመስለኝ አንተ ከኔ ይበልት ታውቃለህ። እኔ በሃይኖቶች ጥናት መስክ ገና የዩኒቨርሲቴ ተማሪ ስሆን አንተ ግን ትልቅ ኢንጂነር ነህ . . ደግሞም መልስ ማለት የገዛ መንፈሳችንና የገዛ ሕይወታችን የሚሰጠን መልስ ነው። የትኛውንም ምላሽ ቢሰጥህ እንኳ የገዛ ራስህ መንፈስና የአስተሳሰብህ አካል እስካልሆነ ድረስ ምን ትርጉም ሊሰጥህ ይችላል?
-መንገድ ላይ ያገኘሁትንና ደስተኛ መሆኑን የነገረኝን ሽማግሌ አስታወስከኝ። ልክ አንተ አሁን የምትለኝ ነበር ያለኝ።
-የሕይወት ተሞክሮና ዕውቀት ያለው ሰው የሚናገረውን ዓይነት መናገር የምችል ጥበበኛ ነህ ብለህ ገመትከኝ ወይስ ትርጉም የሌለው ነገር በመናገር የምፈላሰፍ አደረከኝ! ለማንኛውም መልሱ ወደ መልሱ ለመድረስ በቁርጠኝነትና በጽናት ጥረት ማድረግ ነው።
-ልክ የሽማግሌው ዓይነት አነጋገር ! ምን ለማድረግ ነው ቁርጠኛ የምሆነው?
-እነዚህን ጥያቄዎች መልሰህ በሕይወትህ ደስተኛ ለመሆን ቆርጠህ ትነሳለህ . . የጆርጅን ዓይኖች ትኩር ብሎ አየና ፡- እስኪ ጥያቄ ላቀርብልህና ከየት ነው ምላሹን የምናገኘው?
-ወደ ሐኪሙ ንግግር ተሸጋገርክ! ልክ እንደ ዶክተሩ ሆንክ !
-አሃ፣አንተ እኮ የእንቆቅልሾች ስብስብ ነህ፣ስለ የትኛው ሐኪም ነው የምትናገረው? ሽማግሌው ሐኪም ነው?
-ይቅርታ፣በጣም የታከተኝ መሰለኝ፣አይደለም ሽማግሌው አይደለም። ደስተኝነትን ለማግኘት አንድ ሐኪም ዘንድ ሕክምና እየተከታተልኩ ነው። አነዚህ ጥያቄዎች ብዙ አደከሙኝ፣አንከራተውኛል፤ጭንቀትና ውጥረት ውስጥ ከተውኛል፡፡
-በጥያቄዎቹ ምክንያት የደረሰብህ ጭንቀትና ሃሳብ ሐኪም እስከ ማስፈለግ ደረጃ አደርሶሃል ማለት ነው?! አሁንም ደግሜ አረጋግጥልሃለሁ፣ከራስህ መንፈስና ከሕይወትህ ውጭ የሚመጣ መልስ የለም። ለመሆኑ የሐኪሙን ንግግር የሚመስለው ምኑ ነው?
-መልስ ለመፈለግ ከመነሳታችን በፊት መልሱን ከየት ማግኘት እንደምንችል መወሰን አለብን ነበር ያለው።
-በኔ አመለካከት ይህ በጣም ጥሩና ቀለል ያለ አቀራረብ ነው። ቀለል ያለ አቀራረብ የስኬትና ወደ እውነታ የሚያደርስ መክፈቻ ቁልፍ ነው። ውስብስብነት የውድቀት፣ የደካማነትና የግራ መጋባት ምልክት ነው። ያንተ ሐኪም ምክንያታዊና በጣም ጥሩ ሰው ይመስላል፣እንደዚያ ነው ወይ?
-እርግጥ ምክንያታዊ ነው፣በጣም ጥሩ ሰው ግን አይመስለኝም፣ የማይመች ዓይነት ሰው ከመምሰሉም በላይ ጨዋነትም የሚያንሰውም መስለኛል።
-ታዲ ምን ልታድርግ አሰብክ?
-አላወኩም፣ውጤቱን እስከማይ ድረስ ከርሱ ጋር ለመቀጠል አስቤያለሁ። ይሁንና መልሱን ከዬት ነው የምናገኘው? መልስልኝ
-ይቅርታ፣ሐኪሙን መቃረን አልፈልግም፤ሐኪሙ ምን አለህ?
-አንተ ራስህ ፈልግአለኝ አለኝ። መልሱን ከየት እናገኛለን? መልሱ ትክክለኛ ስለመሆኑ ዋስትናው ምንድነው? የሚል ትያቄ አቀረበልኝ።
-ውብ፣ድንቅ፣ቀለል ያለና ጥልቀት ያለው ጅምር ነው። የሐኪሙን አመለካከት ለመገምገም እኔ ሐኪም አይደለሁም!
-መልሶቹን ከየትነው ማግኘት የሚቻለን?
-ሃይማኖቶችን በመመርመር በገዛ መንፈስህ ውስጥ ፈልግ።
-በሃይማኖቶች ውስጥ !!
-አዎ . . በሃይማኖቶች ውስጥ። በሃይማኖቶች ውስጥ ካልሆነ በኤቲዝም ውስጥ እንድንፈልግ ትፈልግ ኖሯል?!
-ሃይማኖት አልቦነትን . . ኤቲዝምን አምርሬ ነው የምጠላው! የአእምሮና የዕውቀት እንከን ነው።
-ስለዚህም በሃይማኖቶች ውስጥ መፈለጉ ግዴታ ነው ማለት ነው።
-በተለያዩ አመለካከቶችና ሃይማኖቶች ወደ ተሞላችው ሕንድ የሚጓዝበት አጋጣሚ ሳይኖረኝ አይቀርም፡፡ ወደዚያ የማደርገው ጉዞ ከተለያዩ የእምነት ስልቶች ጋር ለመተዋወቅ ይረዳኝ ይሆን?
-ለመተቸት ወይም ትክክል ነው ለማለት እኔ ዶክተር አይደለሁም፣ዶክተሩን መጠየቅ ትችላለህ። የራሴን ግልጽ አስተያየት ግን ሊነግርህ እችላለሁ ፡- የተለያዩ ርእዮቶች፣ ሃይማኖቶችና ጎራዎች ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡበትን መንገድ መተዋወቅ በጣም ጥሩ ነገር ነው። መንገዱ ቀላል፣ገር፣ምክንያታዊ፣ተጨባጭና መንፈስና ሕይወትን የሚያረካ በሆነ መጠን መልሱ ለትክክለኛነት ይበልጥ የቀረበ ይሆናል።
-አመለካከቶችንና ሃይማኖቶችን መመርመር የምችለው እንዴት ነው?!
-የኔ አስተያየት በመጀመሪያ አጠቃላይ የሆነ ምልከታ እንድታደርግ ነው።
-እንዴት ማለት?!
-ሁለት ስልቶችን ማየት እንችላለን። ከአፍታ በፊት እንደ ተነጋገርነው በሃይማኖት ላይ የተመሰረተ ስልትና በኤቲዝም ላይ የተመሰረተ ስልት ናቸው። እኔ ያለ አንዳች ማመንታት በሃይማኖት ላይ ከሚመሰረተው ስልት ጋር ነኝ፣የሃይኖቶች ጥናት ተማሪ ነኝ ብየህ የለም?
-የቀረበውን ምግብ እንዳትበላ ላውክህ አይገባም። የበዛሁብህ መሰለኝ፤እውነቱን ለመናገር እገዛህ ለኔ በጣም አስፈጊ ነው። ምናልባት ግንኙነታችን ገና አዲስ ስላንተ ያለኝ እውቀትም ጠለቅ ያላለ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በንግግርህ በጣም የተደሰትኩ በመሆኔ ምቾት እንዳልነሳህ ተስፋ አድርጋለሁ።
-አይ፣በፍጹም ምቾት አትነሳኝም። የተደረገልኝ የራት ግብዣ ብቻ በቂዬ ነው፣በተለይ ደግሞ ግብዣው በደስተኝነት ሬስቶራንት ! ዋናው ነገር መብላትህ ነውና፣ብላ።
-የሃይማኖቶቹ ስልት ከኤቲዝም ስልት የተሸለ የሚሆነው ለምንድነው? በነገራችን ላይ ሐኪሜ ሁሉንም ሃይማኖቶች የሚያስተባብልና የሚሳለቅባቸው ኤቲስት ነው።
-ከአነጋገርህ እንደገባኝ ምርጥ ሐኪም ከመሆኑ ጋር፣ ኤቲስቶች ከሰው ሁሉ ይበልጥ ዕድለቢሶችና ከገዛ ራሳቸው ራሳቸው የሚሸሹ ሰዎች ስለመሆናቸው ግን በታም እርግጠኛ ነኝ። ለምን የሃይማኖት ስልት ሆነ የኤቲዝም ስልት ለምን አልሆን የሚለውን በተመለከተ ዝርዝሩ ብዙ ሲሆን በሚከተሉት ነጥቦች ማጠቃለል ይቻላል ፡- አንደኛ ለምን እንደ ተፈጠርን የሚያውቅ ከፈጣሪያችን ውጭ ማን ሊያውቅ ይችላል? በሌላ አገላለጽ እኔም ሆንኩ አንተ፣ከራሱ ከፈጣሪው ካልሆነ በስተቀር ለምን እንደ ተፈጠርን ማወቅ አንችልም ማለት ነው። የኤቲዝም ስልት የፈጣረን ጌታ አምላክ መኖሩን ያስተባብላል። ሁለተኛ ፡- ኤቲዝም በሚያቀርባቸው ነገሮች ሁሉ ራሱን በራሱ ይቃራናል። ፍጥረተ ዓለሙ እጅግ በተራቀቁ፣የጸኑና የማይለወጡ በሆኑ ሕግጋት ይመራል፣ይህ የተራቀቀ ሥርዓት ያስገኘው ፈታሪ ሳይኖር በአጋጣሚ የተፈተረ ነው ብሎ ያምናል። ሦስተኛ፡- ኤቲስቶች ብዙውን ጊዜ በፈጣሪ ማመናቸውን እውስጣቸው ይደብቃሉ፤አደጋ ሲደርስባቸውና ችግር ሲያጋጥማቸው ግን መጀመሪያ የሚያድርጉት ያድናቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር
መወትወት ነው። አራተኛ፡- ግልጽ ባለ ሁኔታ ልጠይቅህና ኤቲዝም እውነታ ነው ወይስ ወደ ከንቱነትና ወደ መንፈስ ባዶነት የመሸሽና የመፈርጠጥ ሙከራ ነው?
-ከነዚህ አንዱ እንኳ በቂ ሲሆን ሦስቱም ተጠቃለው አንድ ላይ ሲገኙ ምን ሊኮን ይችላል ! ሙሉ በሙሉ ካንተ ጋር የምስማማ ይመስለኛልና መቀጠል አያስፈልግህም። ኤቲዝም ባለቤቱ ራሱን ከግንዛቤ ውጭ በሆነው የማያምን ሳይንሳዊ አድርጎ የሚወስድ ቅዠት ሲሆን እውነታው ግን አእምሮና ዕውቀትን የሚጻረር ሌሎችን ከመዋሸት በፊት ራስን መዋሸት የሚያሰፍን መሆኑ ነው። ዋነኛው ጉዳይ ግን ከሃይማኖቶች መካከል የትኛውን እንከተል? የሚለው ነው። የሃይማኖቶች ቁጥር በሕይወት የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ያህል ነው . . ሳቀና ፡- ምናልባት ከዚያም ሳይበዛ አይቀርም !
-ሙሉ በሙሉ ካንተ ጋር እስማማለሁ። አሁን ያሉት ሃይማኖቶች ቁጥር ከአስር ሺህ በላይ ነው ይላሉ። እንደ ክርስትና ባለ አንዱ ሃይማኖት ውስጥ ብቻ 33830 የተለያዩ ሴክቶች (ፈለጎች) ይገኛሉ። ይሁንና በአጠቃላይ ምልክታውን ብንቀጠልበትስ ?!
-ምን ማለት ነው የፈለከው?
-በአጠቃላይ ምልከታው ስልቶቹን አማኞችና ኢአማኝ ኤቲስቶች ብለን በሁለት ከፍናል፣አይደለም?
-ልክ ነው።
-በአጠቃላይ ምልከታው መሰረት ሃይማኖቶችና እምነት በሁለት ይከፈላሉ ፡- ወይ ስልታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ መለኮታዊ ሃይማኖቶች ናቸው፣ወይ ደግሞ ስልታቸው ሰው ሰራሽ የሆነ ምድራዊ ሃማኖቶች ናቸው።
-ማለት የፈለከው ገብቶኛል። ባንተ አስተያየት ከሁለቱ የትኛው ነው የሚሻለው?
-የኔን አስተያየት ወደ ጎን በለውና ወደ ሕንድ እጓዛለሁ ብለህ የለ?
-አዎ፣ታዲያ ከርእሳችን ጋር ምን ያገናኘዋል?
-አገረ ሕንድ በምድራዊና መለኮታዊ አመለካከቶች፣ ሃይማኖቶች፣ፈለጎች፣ጭፍሮችና ቡድኖች የበለጸገች ናት። በመሆን እዚያ በመለኮታዊ ሃይማኖቶች ተከታዮችና በምድራዊ ሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል ንጽጽር ማድረግና በገለጻ ሳይሆን በተጨባጭ እውነታውን ማየት ትችላለህ።
-በዚህ ነጥብ ላይ የጠራ አመለካከት ቢኖረኝም፣ጉዳዩን ከሕንድ እስከሚመለስበት ጊዜ ድረስ ማዘግየቱ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን ይህ አቀራረብና ስልት ወደ ምላሹ ሊያደርሰኝ ይችላል ብለህ ታምናለህ?
-ወደ አውነት መመራት፣ለዚያ መታደልና እርግጠኝነትን መጎናጸፍ የእግዚአብሔር ችሮታና ጸጋ ነው። በፍለጋህ ፍጹምና እውነተኛ ከሆንክ ወደምትፈልገው ትደርሳለህ ብዬ አምናለሁ። ዋናው ነገር እውነተኛ ፍላጎት እንዲኖርህና ቆርጠህ በጽናት መቀጠልህ ነው። ነገሮችን በተወሳሰበ ሁኔታ ሳይሆን ቀለል ባለ ሁኔታ፣በትካዜ ሳይሆን በደስተኝነት ስሜት የምታስኬድ ስለመሆንም እርግጠኝነት ይኑርህ።
-ወደ አረጋዊው ሽማግሌ አነጋገር ተመለስክ !
-ይህን ሽማግሌ ዬት ይሆን የማገኘው? በታም አጓጋሀኝ።
-አላውቅም፣በውነት አላውቅም። በታም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩ አርሱ ነበር ስልክ ቁጥሬን የወሰደውና እደውላለሁ ያለኝ፤እኔ አድራሻውን አልተቀበልኩትም። በነገራችን ላይ ቁጥርህንና ኢሜይልህን ትሰጠኛለህ?
-አዝናለሁ፣እንደምታውቀው እኔ ተራ አስተናጋጅ ነኝና የምሰጥህ ቢዝነስ ካርድ የለኝም !
-ግድየለም፣ከሕንድ እንደተመለስኩ ወዲያውኑ እንገናኛለን፣ ተስማማን?
-ተስማምተናል።