ጄፍሪ ላንግ

quotes:
  • እኔ ራሴን ከማውቀው ይበልጥ ያውቀኛል
  • ‹‹ቁርኣን - ይህ ቅዱስ መጽሐፍ በኃይል ምርኮኛው አድርጎኛል፤ልቤ ውስጥ ነግሶ ለአላህ እጅ እንድሰጥም አስገድዶኛል። ቁርኣን አንባቢውን ለብቻው ሆኖ ከፈጣሪው ፊት የቆመ ሆኖ እንዲሰማው በማድረግ ወደ ዋነኛው ነጥብ ይወስደዋል። ቁርኣንን የምር በምትወስድበት ጊዜ በዘበት ማንበብ አይቻልህም፤ባንተ ላይ መብት ያለው ይመስል ጫናውን ያሳርፍብሃል! ይከራከረሃል፣ይተቸሃል፣ያሳፍረሃል፣ይፈታተነሃልም . . ከተቃራኒው ጎራ ነበርኩና ቁርኣንን ያስተላለፈው (በራእ የገለጠው) እኔ ራሴን ከማውቀው ይበልጥ ያውቀኝ እንደነበረም በግልጽ ታየኝ . . ቁርኣን ዘውትር በአስተሳሰቤ ከኔ ይቀድም ነበር፤ጥያቄዎቼንና ተቃውሞዎቼን አሰፍር በነበርኩበት እያንዳንዱ ሌሊትም ጥያቄዎቼን ያስተናግድ ነበር፤እናም በሚቀጥለው ቀን ምላሾቹን አገኝ ነበር። በቁርኣን ገጾች ውስጥም ከራሴና ከነፍሴ ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጫለሁ።››


  • የመንፈስ ባዶነትን መምላት
  • ‹‹በግል ሕይወቴ አንድ ወቅት ላይ፣በጭንቀትና በውጥረት ብዙ ስሰቃይ ከቆየሁና የውስጤን ባዶነት ለመሙላት ከፍተኛ ዝግጁነት ከተሰማኝ በኋላ፣አላህ በወሰን የለሽ ዕውቀቱና በችሮታው ጸጋውን አድሎኝ ሙስሊም ሆንኩ። ከመስለሜ በፊት በሕይወቴ ውስጥ የፍቅርን ትርጉም የማውቅ አልነበርኩም። ቁርኣንን ባነበብኩ ጊዜ ግን የበዛ የእዝነት የርኅራሄና የመተሳሰብ ጎርፍ ሲያጥለቀልቀኝ ተሰማኝ። ልቤ ውስጥም የፍቅር ዘላለማዊነት ስሜት ሲሰርጽ ይሰማኝ ጀመር። ወደ እስላም የመራኝም ሊቃወሙት የማይቻለው የአላህ ፍቅር ነው።››




Tags: