አርኖልድ ቶይንቢ

quotes:
  • ሃይማኖት ሕይወት ነው
  • ‹‹ሃይማኖት ወሳኝ ከሆኑ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ተሰጥኦዎች አንዱ ነው። የሃይማኖት እጦት አንድን ሰው፣ምኑም የራሱ ካልሆነ ገበታ ላይ ሃይማኖታዊ ማጽናኛ ፍለጋ ለመሄድ ወደሚያስገድደው የተስፋ መቁረጥና የመንፈስ ዝቅጠት ሁኔታ ያስገባዋል።››


  • የሰው ልጆች ሁሉ መምሕር
  • ‹‹የዐረባዊው ነቢይ የሕይወት ታሪክ የተከታዮቹን ልብ ማርኮ ይዟል። ሰብእናውም እነሱ ዘንድ ወደ ሰማየ ሰማያት መጥቋል። በመሆኑም ወደርሱ የተላለፈውን ሁሉ እንዲቀበሉ የሚያደርጋቸውን እምነት በመልክቱ አምነዋል። በሱንና እንደ ተጠናቀረው ሁሉ ተግባራዊ ክንዋኔዎቹም የሕግ ምንጭ ሲሆኑ፣ይህም የእስላማዊውን ማህበረሰብ ሕይወት አቀናጅቶ በመምራት ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ድል አድራጊ ሙስሊሞች ሙስሊም ካልሆኑ ዜጎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነትም የሚገዛ ነው።››


  • የሙሐመድ ነቢይነት መልክት
  • ‹‹ሙሐመድ በዐረባዊው ማሕበረሰባዊ አካባቢ የሚከተሉትን ሁለት ገጽታዎች በማስፈን ተልእኮውን እውን ለማድረግ ነው ሕይወቱን የሰጠው። እነሱም፦ ሃይማኖታዊ ፍካሬን በተውሒድ ላይ የማነጽና አስተዳደርን በተመለከተ ሕግና ሥርዓትን የማስፈን ገጽታዎች ናቸው። ምስጋና ተውሒድና የአስፈጻሚ ስልጣንን አጣምሮ ለያዘው የእስላም አጠቃላይ ሥርዓት ይሁንና ይህ በተግባር ተፈጽሟል። በዚህም ምክንያት እስላም ዐረቦችን ከማይም ሕዝብነት ወደ ስልጡን ሕዝብነት ያሸጋገረ ወደፊት የሚፈናጠር ኃያል ጥንካሬ ሊያገኝ ችሏል።››


  • ተሸናፊ አሸናፊውን ማረከው!!
  • ‹‹በመስቀል ጦርነቶች ተሸናፊው እስላም አሸናፊዎቹን ማርኳል። የዛገ ላቲናዊ ሕይወት ወደነበረው ወደ ክርስቲያኑ ዓለም ሕይወትም የስልጣኔ ዓይነቶችን አስገብቷል። በአንዳንድ ሰብአዊ እንቅስቃሴ መስኮች፣ለምሳሌ በኪነ ሕንጻ በመካከለኞቹ ክፍለ ዘመናት እስላማዊው ተጽእኖ በመላው የክርስቲያን ዓለም ስር የሰደደ ነበር። በሲስሊና በአንደሉስ ደግሞ ጥንታዊው ዐረባዊ ኢምፓይር በአዲሱ ምዕራባዊ መንግስት ላይ ያሳረፈው አሻራ ሰፊ፣ጥልቅና አጠቃላይ ነበር።››




Tags: