{፦ ኑ፤ጌታችሁ በናንተ ላይ እርም ያደረገውን ነገር (በርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ በላቸው፤በርሱ (በአላህ) ምንንም ነገር አታጋሩ፤ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ)፤ልጆቻችሁንም ከድኽነት ፍራቻ አትግደሉ፤እኛእናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና፤መጥፎ በሥራዎችንም ከርሷ የተገለጸውንም የረደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፤ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጅ አትግደሉ፤ይሃችሁ ታውቁ ዘንድ (አላህ) በርሱ አዘዛችሁ። የየቲምንም ገንዘብ፣ብርታቱን (አካለ መጠን) እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፤ስፍርንና ሚዛንንም በትክክል ምሉ፤ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም፤በተናጋራችሁም ጊዜ፣በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ፣(እውነትን በመናገር) አስተካክሉ፤በአላህም ቃል ኪዳን ምሉ፤ይኻችሁ ትገሠጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ። ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ተከተሉትም፤(የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፤ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና። ይኻችሁ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ።}[አል አንዓም፡151-153]
በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{አላህ በማስተካከል፣በማሳመርም፣ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፤ከአስከፊም፣(ከማመንዘር)፣ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ከመበደልም ይከለክላል፤ትገነዘቡ ዘንድ፣ይገሥጻችኋል።}[አል ነሕል፡90]
ለውሸት፣ለግድያ፣ለግፍ፣ለበደል፣ለስርቆት፣አስገድዶ ለመድፈር፣ወላጆችን ለማስከፋትም ሆነ ለመሳሰሉት እኩይ ነገሮች ጥሪ የሚያደርግ ሃይማኖት ትክክለኛ ሃይማኖት ሊሆን አይችልም።
{ከርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትግገዙም፤አላህ በርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም፤ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤እርሱን እንጅ ሌላን እንዳትግገዙ አዟል፤ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፤ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።}[ዩሱፍ ፡40]
ያ ሃይማኖት የሰው ልጅ ፈጣሪውን አስመልክቶ የሚኖሩበትን ግዴታዎች ማደራጀት፣በሰዎች መካከከል የሚኖሩትን ግንኙነቶችም ሥርዓት የሚያስይዝ መሆን ይኖርበታል። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{አላህንም ተገዙ፤በርሱም ምንንም አታጋሩ፣በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣በየቲሞችም፣በምስኪኖችም፣በቅርብ ጎረቤትም፣በሩቅ ጎረቤትም፣በጎን ባልደረባም፣በመንገደኛም፣እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው (ባሮች)፣መልካምን (ሥሩ)፤አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም።}[አል ኒሳእ፡36]
አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{የኣደምንም ልጆች በእርግጥ (ከሌላው ፍጡር) አከበርናቸው፤በየብስና በባሕርም አሳፈርናቸው፤}[አል እስራእ፡70]
በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{እላንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤እንድትተዋወቁም ጎሣዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤አላህ ዘንድ በላጫችሁ፣በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤አላህ ግልጽን ዐዋቂ፣ውስጥንም ዐዋቂ ነው።}[አል ሑጁራት፡13]
ጋኔን (ጅንን) ቁርኣንን አዳምጦ እርስ በርሳቸው የተባባሉትን ሲነግረን አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{አሉም ፦ ሕዝቦቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን መጽሐፍ፣በፊቱ ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ፣ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራ የኾነን ሰማን።}[አል አሕቃፍ፡30]
በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{ከቁርኣንም፣ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፤በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም።}[አል እስራእ፡82]
ቁርኣን ከማይምነትና ከጥመት ጨለማ ወደ አላህ ተገዥነትና የሁለቱም ዓለማት ተድላ ሰዎችን የሚወስድ መሪ ብርሃን ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ፣ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ። ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ።}[አል ማእዳህ፡15]
በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ብሏል፦
{በሃማኖት ማስገደድ የለም፤ቅኑ መንገድከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፤በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው፣ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፤አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው። አላህ የእነዚያ ያመኑት ሰዎች ረዳት ነው፤ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል፤እነዚያም የካዱት ረዳቶቻቸው ጣዖታት ናቸው፤ከብርሃን ወደ ጨለማዎች ያወጧቸዋል፤እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፤እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው።}[አል በቀራህ፡256-257]