ግጭት . .

ግጭት . .

ግጭት . . (1)

- ሰዓቱ ሁለት ተኩል ነው፣የጊዮርጊስን ቀጠሮ ማክበር እንችል ይሆን?

- ቁርሱን ቶሎ እንብላና እንቀሳቀሳለን፤መንገድ እንደ ጀመርን ትደውልለትና ጥቂት ልንዘገይ እንደምንችል ትነግረዋለህ። ትናንት ትንሽ ጠንከር ቢልብኝም ጊዮርጊስ ጨዋ ሰው ነው፣ችግሩን ይረዳልናል።

- ትንሽ ጠንከር ቢልብኝም ነው ያልከው?!

- ስላንተ ጉዳይ ትናንት ደውሎልኝ ማለት የሚችለውን ሁሉ ነው ያለኝ።

- በተፈጠረው ነገር የተሰማኘን ሀዘን አሁንም ደጋግሜ እገልጻለሁ።

- ስምምነታችንን ማፍረስ ፈልገሃል ልበል?

- አይደለም፣ጀማል ከልብ አመሰግነሃለሁ፣ውለታህን መዘርዘር ይሳነኛል።

ጆርጅና ጀማል ወደ ዓለም አቀፍ ሠራተኛ ኤጀንሲ ኩባንያው ደረሱ

ጊርጊስ መኖሩን ሲጠይቅ እየጠበቀው መሆኑን ጸሐፊው ነገረው
። አብረው ገቡና ጊዮርጊስ በሰላምታ ተቀበላቸው . .

 

- የምስራች ንገረና . . ወዳጅህ ቦርሳውን አመጣልህ?!

- ተወን መጀመሪያ እንቀመጥ፣ሁለተኛ በመዘየግቴ ይቅርታ አድርግልኝ።

- ጀማል የሚባለውን ወዳጅህን ትናንት እስከ አንገቱ ነው የነገርኩት። እውነቱን ለመናገር ግን ከአነጋገሩ ጨዋ ሰው ስለመሰለኝ ይሰርቃል ብዬ አልገምትም፣ግን ብዙ ጫና አድርጌበታለሁ።

- አዝናለሁ፣አንተንም አልፍቻለሁ፤ይቅርታ አድርግልኝ፣ትምረናለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ጀማል ድንቅ ሰው ነው ይቅር ብሎኛል፤ቦርሳዬን ሆቴሉ መጸዳጃ ቤት ውስጥ አግኝቸዋለሁ!

- ወየው፣ጌታችን በእዝነትህ ድረስልን! አላህ ለኔም ላንተም ይቅር ይበለን እንጂ በሸካራ አቀራረብ ጀማልን ብዙ ተናግሬዋለሁ!

- ይህ ወዳጄ ጀማል ነው፣ተዋወቀው።

- ውይ! ወንድሜ ትናንት ለፈጸምኩብህ ነገር ይቅርታ እለምነሃለሁ።

- ችግር የለውም፣አላህ ይቅር ይበልህ . . በቃ ነገሩ አብቅቷል፣ረስተን ልንዘጋውና ላናነሳው ከጆርጅ ጋር ተስማምተናል።

- ጆርጅ ቦርሳውን ማግኘቱን መቼ ነበር ያወቅከው?

- በቦርሳው ምትክ የባለቤቴን ወርቅ ይዤለት ስመጣ ጧት ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ ነበር።

- አላህ ሆይ ምህረትህን ለግሰን፤ጀማል ደጋግሜ ይቅርታ እጠይቀሃለሁ። አላህ እንዲህ ብሏል እኮ ፦ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስሕተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ።} [አል ሑጁራት፡6]

- ይህ የምን ጥቅስ ነው?

- የቅዱስ ቁርኣን ጥቅስ ነው።

- የአገሩ ክርስቲያኖችም ቁርኣንን በቃላቻው ያውቁታል ማለት ነው?

- ትናንት ያስደስትህ ይሁን አይሁን ባላውቅም ነገ ያልተጠበቀ ነገር እነግረሃለሁ ብዬ አልነበረም! እኔ ከሰለምኩ ገና ስድስት ወሬ ነው።

- ክርስትናን ትተህ ሰለምክ?!

- አዎ . . ምን ያስገርማል? ብዙዎች ናቸው እስላምን ተቀብለው የሚሰልሙት። እንዳውም እስላም በዓለም ላይ ከሁሉም ይበልጥ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ የሚገኝ ሃይማኖት ነው።

- የሚገርም ነገር የለውም፣ ግን ሙስሊም ያልሆነ ሰው ሲሰልም ማየት ለኔ ይህ የመጀመሪዬ ነው።

ጀማል በአድናቆት እጁን ራሱ ላይ አድርጎ . .

- ወንድሜ ስትለኝ ገርሞኝ የዜግነትና የሰብዓዊነት ወንድም ለማለት የፈለክ መስሎኝ ነበር፤ወንድሜ ለዛሬውና ለመጪው ዘላለማዊ ሕይወት መታደል በመብቃትህ እንኳ ደስ አለህ።

- ለዛሬውና ለወዳኛው ዘላለማዊ ሕይወት መታደል! የወዳኛውን ዘላለማዊ ሕይወት እንኳ አላውቅም፣በዛሬው ሕይወት መታደልን ማግኘት የሚቻለው ግን እኛ ዘንድ በምዕራቡ ዓለም ነው።

- ቁሳዊ ደስታና ብልጽግናን ለማለት ፈልገህ ከሆነ ልክ ነህ።ሕሊናዊ ደስታና መንፈሳዊ ተድላን በተመለከተ ግን ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እተባባሰና ችግሩ እየከፋ በመሄድ ላይ ነው። ለዚህ ነው በምዕራቡ ዓለም ራሳቸውን የሚያጠፉ፣በመንፈስ ጭንቀት የሚሰቃዩና ለተለያዩ የስነ ልቦና ችግሮች የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀብ ሲሄድ የሚስተዋለው።

- ጀማል እኔን ማለትህ ነው?

- አልገባኝም! ከጠቀስኳቸው ነገሮች ጋር አንተን የሚያገናኝ ምን አለ?

- እኔም የዚህ የምትናገረው ምዕራቡ ዓለም አካል ነኝ።

- ጉዳዩ ስለ መታደል ምንነት ነው። ውስጣዊው ህሊናዊ ደስታ፣ደስታ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው። ከመንፈሳዊነት የተራቆተ ቁሳዊ ሕይወት የግንዛቤ ብዥታ የፈጠረ ይመስለኛል፤እናም ለአለመታደል ምክንያት ሆኗል።

- አላህ ይመስገን እንኳን ቦርሳህን አገኘህ እንጂ አሁን ጉዳያችን ስለ መታደል ሳይሆን ለቃለ መጠይቁ ስለሚጠብቁን ሰዎች ናውና ሥራ አለብን።

- ልክ ነህ . . ይቅርታ እኔ ትቻችሁ ልሂድ . . ጆርጅ መቼ ተመልሼ ልውሰድህ?

- ሥራው የሚያቆየኝን ይመስለኛልና ዛሬ አንተ እረፍና ስንጨርስ እኔ ራሴ ወደ ሆቴሉ አደርሰዋለሁ።

- አመሰግናለሁ . . ጀማል መልካም ፈቃድህ ከሆነ ነገ ሁለት ሰዓት ላይ ብንገናኝ ደስ ይለኛል።

- ተስማምተናል፤በሉ አሰላሙ ዓለይኩም ወረሕመቱሏህ ወበረካቱህ።

- ጀማል ድንቅ ሰው ነው፣ እንዴት ነው የተዋወቅከው?

- እንግሊዝ አገር በሚገኘው ወንድሙ በኩል ነው። በነገራችን ላይ ጠንከር ብለህ እንደተቆጣኸው ቢናገርም ከመምጣታችን በፊት ስለ አንተ ስናነሳ ግን ጨዋ የሆነ በጣም ጥሩ ሰው ነው ሲለኝ ነበር፣ክርስቲያን ነህ ብሎም ያስብ ነበር።

- እስላም ውስጥ ለጠላቶቻችን ቢሆን እንኳ ፍትሕ አስተካካዮች እንድንሆን ታዘናል። ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል ፦ { . . ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፤አስተካክሉ፤እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ የቀረበ ነው። አላህንም ፍሩ። አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።} ]አል ማኢዳህ፡8[ አሁን ይህን እንተውና በመጀመሪያ ስለ ሥራ ውሎቹ መነጋገር ያስፈልገናል፣ከዚያ ቃለ መጠይቁን ትጀምራለህ። እንደ ተረዳሁት ያለህ ጊዜ አጭርና ጠባብ ነው።

- ልክ ነህ፣በኋላ ላይ ግን ስለ መስለምህ ጉዳይ ካንተ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ።

- በምሳ ሰዓት ወይም ወደ ሆቴሉ ስንመለስ መንገድ ላይ ሊሆን ይችላል።

ማታ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ጆርጅና ጊዮርጊስ በጊዮርጊስ መኪና ወደ ሆቴሉ ለመሄድ የሠራተኛ ኤጀንሲ ኩባንያውን ለቀው ወጡ። ያሳለፉት ቀን ምልምሎቹን ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ውሎችንና ስምምነቶች በመፈራረም . . ሥራ የበዛበት ቀን ነበር።

- በአንድ ቀን ይህን ሁሉ ለመስራትና የቀረቡትን ሁሉ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ችለሃል። ቃለ መጠይቁን እንዴት አገኘኸው?

- እውነቱን ለመናገር ከጠበቅኩት በላይ ጥሩ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። ከሙያዊ ጉዳዮች ባሻገርም ማህበራዊ ስነ ምግባራቸው አድናቆት ጭሮብኛል። እንዲህ ያለውን ነገር እንግሊዝ ውስጥ አልለመድነውም፤በናንተ ጥረት ተልእኮዬ ቀላልና ስኬታማ የሚሆን ይመስለኛል።

- ቀጣይ እርምጃ ምንድነው የሚሆነው?

- መቻኮል አልፈልግም፣ነገና ተነገወዲያ ከሌሎች ሁለት ኤጀንሲዎች ጋር ሠራተኞችን ቃለ መጠይቅ ማድረግ ይጠብቀኛል፤ከዚያ በኋላ ነው ተገቢውን የምወስነው።

- መልካም፣መቸኮል ደግ አይሆንም፣አይደለም እንዴ?

- በእውነቱ ችግሩን አስታወስከኝ . . ለጀማል ለዚህ ድንቅ ሰው ያለኝን አክብሮትና ባለውለታነቱን ተናግሬ አልጨርሰውም . . መቸኮል ጥሩም አይደለም ብለሃል፣ታድያ ለምንድነው ተቻኩለህ የሰለምከው?

- እህህ፣ለመፍረድ አትቸኩል! ቸኩሏል ያለህ ማነው? እንዲያውም በጣም ዘግይቻለሁ።

- እንዴት?

- እስላምን አምኜ እስክቀበል ድረስ በቂ ጊዜ ወስጄ አጥንቼዋለሁ። ያሳመነኝም የዚህ ኩባንያ ባለቤት ነው፤ግና እንድሰልም ፈጽሞ ጫና አድርጎብኝ፣አዞኝም ሆነ ጨቅጭቆኝ አያውቅም። እስከዚህ ደረጃ ድረስ አልዘገየሁም። የዘገየሁት ሙሉ በሙሉ አሳማኝ ሆኖ ካገኘሁት በኋላ ሳልሰልም ስድስት ወር ሙሉ መቆየቴ ነበር፤በትክክልም ይህ መዘግየት ነው።

- እንዲህ ያለ ከባድ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ስድስት ወር በጣም አጭር ጊዜ በመሆኑ ችኮላ ነው!

- በዚህ ጊዜ ውስጥ ብሞትና የዛሬውንና የወዳኛውን ሕይወት ውርደት ተከናንቤ ቢሆን ኖሮስ?!

- የዛሬውን ዓለማዊ ሕይወትና የወዳኛውን ሕይወት ሁሌ ማያያዛችሁ በጣም የሚገርም ነው፤ይሁንና የዛሬውና የወዳኛው ሕይወት ውርደት ምን እንደሆነ ልታብራራልኝ ትችላለህ?

- የዛሬው ዓለማዊ ሕይወት ውርደትን በተመለከተ፣እስከ ሰለምኩበት ጊዜ ድረስ ውስጣዊ መረጋጋት፣ሕሊናዊ ሰላምና ደስታ ተሰምቶኝ አያውቅም። በዚህ ልትገረም ትችል ይሆናል፣ ግን እውነታው ይህ ነው። ተውሒድ የአላህ ፍጹማዊ አንድነት፣ለርሱ ብቻ ተገዥ መሆን፣ወደርሱ ብቻ መጠጋትና እርሱን ብቻ መማጸን . . ቁሳዊ ችግሮች ቢኖሩ እንኳ እውነተኛውን ውስጣዊ እርካታን ያጎናጽፋል፣ልቦናን ያጠራል። በእርግጥ አንዳንድ ዘመዶቼ አርቀውኛል፣ከዚያም አልፈው ሊጎዱኝም ሞከረዋል።

- ተውሒድ - የአላህ ፍጹማዊ አንድነት - ውስጣዊ እርካታን ያጎናጽፋል? ልቦናን ያጠራል?!

- አዎ . . ጣዖታዊነት፣ሽርክና ፈጣሪ አምላክን አንድም ሦስትም ነው ብሎ ማመን ውስጣዊ ጭንቀትና የልቦና መታወርን እንደሚያወርሱ ሁሉ ተውሒድ ከዚህ ሁሉ ነጻ ያወጣል። በመሆኑም ሌሎች ባእድ አማልክትን ከርሱ ጋር እያጋራሁ ሞቼ አላህን መገናኘት አልፈልግም። አላህ በጣም ርህሩህና መሐሪ በመሆኑ ሁሉንም ኃጢያቶች የሚምር ቢሆንም በርሱ ማጋራትን -ሽርክን- ግን አይምርም። ጌታዬ ለኔ ርህሩህና ቸር በመሆኑ ሳልሰልም እንድሞት አላደረገኝም።

- አነጋገርህ የሚገርም ነው!

- ምኑ ነው የሚገርመው?

- አሁን ወደ ሆቴሉ ስለደረስን ሬስቶራንቱ ውስጥ ጭውውታችንን እንቀጥላለን።

- ወደ ቤት ለመመለስ በጣም ስለ መሸብኝ እባክህን ይቅርታ አድርግልኝና ሌላ ጊዜ እንጫወታለን።

- እናም እራት ብቻየን እባላለሁ ማለት ነዋ!

- የማያስጨንቅህ ከሆነ።

- ግዴለም፣ደህና እደር።

ግጭት . .(2)

ጆርጅ ወደ ክፍሉ ሄዶ እቃዎቹንና ሸዳንጣውን ካኖረ በኋላ በቀጥታ ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ተመልሶ መጣ። በጣም ርቦት ነበር . . እራቱን በመብላት ላይ እያለ ወጣ ያለ እንግዳ ልብስ የለበሰ ሰው ከአጠገቡ ቆሞ አገኘው . .

- ራሚ እባላለሁ እንዳናግርህ ትፈቅድልኛለህ?

- ተቀመጥ።

- ትናንት በአንቡላስ ወደ ሆስፒታል የተወሰድከው አንተ ነህ?

- አዎ።

- እዚህ አገር ሌቦች ስለሚበዙ ተጠንቀቅ።

- አዎ . . ትናንት ስርቆት ተፈጽሞብኝ ነበር።

- አውቄአለሁ፣ለዚህ ነው ያስጠነቀቅኩህ።

- እንዴት አወቅክ?

- በመናፍስት አማካይነት ሁሉንም ነገር አውቃለሁ።

- የምን መናፍስት?

ይህማ የማይነገር የኔ ምስጢር ነው።

- ነገ ምን እንደሚደርስብኝ ታውቃለህ?

- አዎ አውቃለሁ።

- ይህ አባባል ከሰብአዊ አእምሮና ከሃይማኖት ጋር አይጻረርም?

- ከኛ ይበልጥ ሃማኖታችንን ታውቃለህ፣አንተ ሙስሊም ነህ?

- አይደለሁም፣ግን በናንተ ቁርኣን ውስጥ ከህዋስ የራቀውን ነገር ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቅም ይላል።

- ይህ ራሱን የቻለ ዕውቀት ነውና ሁሉንም ሃይማኖቶች ቸል በላቸው።

- እኔ ሙስሊም አይደለሁም፣ግን የምትለው ነገር አፈተረት እንጂ ዕውቀት አለመሆኑን አምናለሁ። እንዲህ ያለው ነገር እኛ ክርስቲያኖች ዘንድም አለ፤እናንተ ሙስሊሞች ዘንድ መኖሩን ግን አላውቅም ነበር!

- እህህ፣ጣሊያን የክርስቲያኖች አገር ናት፣እዚያ ያለው የጠንቋዮች ቁጥር ከሃይማኖት መሪ ካህናት ቁጥር ይበልጣል!

- የተነፈግነውን መንፈሳዊነት ለማግኘት በምናደርገው ፍለጋ ምክንያት አፈተረትና ጥንቆላ በምዕራቡ ዓለም በፍጥነት በመሰራጨት ላይ መሆኑን አውቃለሁ። ይሁን እንጂ አፈተረትና ጥንቆላ ነውና ይህን ዕውቀት ነው ብለህ ልታሳምነኝ ትችላለህ?

- አዎ።

- ትናንት ሁለት ጊዜ ነበር የተሰረቅኩት፤ማን እንደ ሰረቀኝ ታውቃለህ?

- እንዳነበው መዳፍህን ልትሰጠኝ ትችላለህ?

- እንካ።

- በሁለቱም ጊዜ የሰረቀህ ለአንተ በጣም ቅርብ የሆነ ሰው ነው።

- በጣም ጥሩ፣እውነትም ትንቢት የምታውቅ ትመስላለህ፤የተሰረቀብኝ ምንድን ነበር?

- ለአንተ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነው የተሰረቅከው።

- ሰርቆት የት አስቀመጠው?

- ቅርብ ቦታ ነው . . ሩቅ ነው፤ቦታውን ለሚነግረኝ መንፈስ እንድሰጠው አስር ዶላር ብቻ እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ።

- ከኔ የተሰረቀው ቦርሳዬ ያለበትን ቦታ ከነገርከኝ ከቦርሳው ውስጥ መቶ ዶላር እሰጠሃለሁ።

- መጀመሪያ አስሩን ዶላር ስጠኝና።

- አሁን ምንም የለኝም።

- አሁን አስሩን ዶላር ካልከፈልክ ከባድ ችግሮች እንደሚያጋጥሙህ ደጉ መንፈስ ነግሮኛል።

- እህህ፣አሁን ምግቤን ጨርሻለሁ፣ያንተ ደጉ መንፈስ ውሸታም መሆኑን ንገረው፣ቦርሳዬ ከኔ ጋር ነው፣አልተሰረቀም፣በአንተ መጫወት ስለ ፈለግሁ ብቻ ነው።

ጆርጅ አብሮት በነበረው አባይ ጠንቋይ እያሾፈና እየተዘባበተ፣ሮማ ውስጥ ያሉ ጠንቋዮች ከካህናቱ ቁጥር የመብለጣቸው እውነታ ለምን እንደሆነ እየተገረመ ወደ ክፍሉ ሄደ። ሃይማኖት ከስሮ ሎጂክን፣አእምሮንና ሳይንስን በመጻረሩ ረገድ ከአባይ ጠንቋዮችም መብለጡ ይሆን? ትናንት ሳያይ ያደረውን ኢሜይል ለማየት ኮምፒውተሩን ከፈተ . . ከጃኖልካ የተላከ ደብዳቤ አገኘ . .

‹‹ወዳጄ ጆርጅ

መልእክትህን አንብቤ የደረሰብህ ነገር በጣም አሳዝኖኛል።ሁለት ነገሮች ግን ግልጽ ሊሆኑ ይገባል። አንደኛ፦ ሃይማኖታቸው በዚያ ላይ የማያበረታታቸው እስከሆነ ድረስ፣የትኛውንም ሃይማኖት አመለካከትና ርእዮትን ከግለሰብ አቀንቃኞቹ ለይተን መመለከት ይኖርብናል። ሁለተኛ፦ እኔ እዚህ ከሙስሊሞች አብሬ እየኖርኩ ነው። በአጠቃላይ አነጋገር ድህነትና የጎሳ ልዩነቶች ቢኖሩባቸውም፣መንግስታዊ ተቋሞቻቸው ደካማ ቢሆኑም . . ወደዚያ የሚገፋፉ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም ከስርቆት በጣም የራቁ ሰዎች ናቸው። ይህን የሚያደርጉት መንግስትን በመፍራት ሳይሆን ሃይማኖታቸው ስለሚከለክላቸው ብቻ ነው። እኛን ግን ከዚህ የሚከለክለን በአብዛኛው ስርዓቱና ተቋማቱ እንጂ ግብረገብነት ወይም ሃይማኖት አይደለም። ህግና ሥርዓቱ ሲናጋ እኛ ዘንድ ስለሚፈጠረው መዓት ከኔ ይልቅ የምዕራቡን ተሞክሮ አንተ ታውቃለህ። በመጨረሻ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ከአሻፈረኝ ባይነቴም ጋር ለመስለም በጣም የቀረብኩ መሆኔን ነው፤አንዳንድ ጥቃቅን ዝግጅቶችና ስጋቶች ብቻ ናቸው ለጊዜው ከመስለም ያቆሙኝ።

ጃኖልካ››

መልስ ጻፈለት፦

‹‹ወዳጄ ጃኖልካ ላሳየኸኝ አጋርነት አመሰግናለሁ። እውነታውን እንዴት እንደምነግርህ አላውቅም፤የተሰረቅኩ መስሎኝ ሙስሊም ወዳጄን በችኮላ ወንጅየው በደል ፈጸምኩበት። እርሱ ግን በድንቅ ሰብእናው፣በምሉእ ስነ ምግባሩ፣በአስደናቂ ትእግስቱና በትህትናው አሳፈረኝ። ለጅልነቴ እንዴት ብዬ ይቅርታ እንደምጠይቀው ማወቅ እንኳ አቃተኝ! መስለምን በሚመለከት በኔ በኩል ለምን እንደሆነ እንጃ አሁን አመቺ አይደለም የሚል ስሜት አለኝ፤አሁንም ድረስ ያልተመለሱልኝና የሴቶችን ጉዳይ፣ሰብዓዊ መብትንና ሃይማኖቱ ያለውን የሥልጣኔ ደረጃ የሚመለከቱ ነጥቦች ይቀሩኛል። በዚህ ረገድ የምትደርስበትን እንደምታስታውቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ጆርጅ››

በመቀጠል ከሌቪ የተላከለትን ኢሜይል ከፈተ . .

ወዳጄ ጆርጅ

በደረሰብህ ነገር በጣም አዝኛለሁ፤አስጠንቅቄሃለሁ፣አሳስቤሃለሁም። የደረሰብህ ነገር ምናልባት ያንተንና የእጮኛዬን የሐቢብን ወደ እስላም በፍጥነት መንደርደር ለማርገብ መልካም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ልንረዳህ የምንችለው ነገር ካለ አሳውቀን፤ወደ ቴልአቪቭ ብትመጣ ለሁላችንም ትልቅ የምስራች ከመሆኑም በላይ ከአሸባሪዎቹ ሙስሊሞች እጅ አንተን መታደግ ይሆናል፤መምጣትህን በጉጉት እንጠብቃለን።

ሌቪ››

መልስ ጻፈላት፦

ወዳጄ ሌቪ

በጣም ናፍቄሻለሁ፣ምክሮችሽ ሁሌም ያስፈልጉኛል፤ እውነቱን ለመናገር ግን ምን እንደምልሽ እቸገራለሁ . . የሆነው ነገር ሳልሰረቅ የተሰረቅኩ መስሎኝ ሙስሊም ወዳጄን በችኮላ ጠርጥሬ በማስቀየም በደል ፈጸምኩበት። እርሱ ግን በድንቅ ሰብእናው፣በምሉእ ስነ ምግባሩ፣በአስደናቂ ትእግስቱና በትህትናው አሳፈረኝ። ለጅልነቴ እንዴት ብዬ ይቅርታ እንደምጠይቀው ማወቅ እንኳ አቃተኝ! ወደ እስላም አለመንደርደሬን ደግሜ ልገልጽልሽ እወዳለሁ። በእርግጥ በብዙ ሕግጋቱና እምነቶቹ በአድናቆት ብያዝም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን ገና ውሳኔ ላይ አልደረስኩም። ከሐቢብ ጋር በመተጫጨታችሁ እንኳን ደስ አለሽ እላለሁ። እውነት እልሻለሁ በአእምሮ ብስለቱ በዕውቀቱና በሰፊ ግንዛቤው እሱን የመሰለ የትም አታገኚም። ከርሱ ጋር ስትወያዪ የትም ቦታ የማታገኚውን እርሱ ዘንድ ታገኝያለሽ። እናንተ ዘንድ ወደ ቴልአቪቭ ብመጣ ደስታዬ ነበር፣ሆኖም ግን እዚህም እዚያ ያገኘሁት ዓይነት አቀባበልና መስተንግዶ እያገኘሁ ነው፤ምናልባት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እጎበኛችሁ ይሆናል።

ጆርጅ››

ከዚያም ከደረሱት ደብዳቤዎች መካከል የካትሪናን አገኘ . .

‹‹ፍቅሬ ጆርጅ

ትናንት ወደ ሆስፒታሉ ስሄድ በባስም ወንድም የተፈጸመብህን ስርቆት ኣደም ነግሮኝ በጣም ተሰምቶኛል። ለማንኛውም እርሱ የሰረቀህ መሆኑን እርግጠኛ እንድትሆን እፈልጋለሁ። እስላምን እንዲያስተዋውቀኝ ባስምን በጎበኘሁበት ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በቅርበት ለማወቅ እንደቻልኩት፣ወንድሙ እንደ እርሱ ከሆነ ይህንን ይሰራል ብዬ አላምንም፤ለሁሉም ጻፍልን።

መልስ ጻፈላት . .

‹‹የኔ ፍቅር

ምንም ጥርጣሬ በሌለው ማስረጃ እርሱ ያልሰረቀኝ መሆኑን አረጋግጫለሁና አንቺም አርግጠኛ ሁኚ። የሆነው ነገር በኔ በኩል በተፈጸመ ስህተት ምክንያት ነውና ሰለኔ ሆነሽ ባስምን ይቅርታ ጠይቂልኝ። በነገራችን ላይ ካቶሊካዊቷ ሃይማኖተኛ ካትሪና እስላምን ለማወቅ መፈለጓ እንዴት ሊታመን ይችላል?! ወይስ ቁርኣን ወይም ማንበቡን ትፈሪው የነበረውና ‹‹ለኢየሱስ ያለኝ ታላቅ ፍቅር ወደ እስላም ወሰደኝ›› የሚለው መጽሐፍ ተጽእኖ አሳድሮብሽ ይሆን?! የኔማ ፍቅር በጣም ናፍቄሻለሁ።

አፍቃሪሽ ጆርጅ››

ልኮላቸው ለነበረው ጥያቄ ከወዳጆቹ የተላኩለትን ምላሾች ሲያነብ ቆየና ሁሉንም አንድ ላይ ጨመቅ አድርጎ ለያንዳንዳቸው መልሶ ላከ . .

‹‹ሽብርተኝነትን በተመለከተ

ሐቢብ ሽብርተኝነት ፈጽሞ ሃይማኖት የለውም።

ሌቪአባቴን የገደሉ ሙስሊሞች ሽብርተኞች ካልሆኑ ሽብርተኝነት ሌላ ትርጉም አለው ብዬ አላስብም።

ካትሪና እስላም ውስጥ ሽብርተኝነት የለም።

ኣደምሽብርተኛ ሀብት ለመዝረፍ የሌሎችን አገር የሚወር ነው።

ቶምሽብር ተቃዋሚዎችን ለማጥላላትና ለማጥቃት የሚያገለግል አዲሱ ስልት ነው።

ጃኖልካከሽብርተኝነት ዓይነቶች ሁሉ አደገኛው ርእዮተ ዓለማዊ ሽብርተኝነት ነው። ይህም በነጻ ማሰብንና የገዛ አእምሮ መጠቀምን እንኳ ማስፈራራትና መከልከል ነው። እስላም ግን በነጻ ለማሰብና ለማስተንተን ጥሪ ያደርጋል።

ጆርጅ በኛ በምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን በኩል ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣በእስላምና በሽብርተኝነት መካከል እስካሁን ምንም ግንኙነት አላየሁም።

ሴቶችን በተመለከተ

ካትሪና ስለ ሕጃብ እስካሁን መረዳት ባልችልም፣ሴት ልጅ እስላም ውስጥ በእጅጉ የተከበረች ናት።

ሌቪከአይሁዳዊነትም ሆነ ከክርስትና የከፋ አይደለም።

ቶምበዚህ ርእስ ላይ ተጨማሪ ጥናትና ምርምር ማድረግ ያስፈልገኛል። ቁርኣን ውስጥ {ወንድም እንደ ሴት አይደለም፤} ]ኣል ዒምራን፡36[ የሚል ጥቅስ ሰፍሯል።

ሐቢብአልበደላትም።

ጃኖልካበኛ ባህል ውስጥ በሁለቱ መካከል ግልጽ ልዩነቶች ከመኖራቸውም ጋር፣ተመሳሳይነት በሌለበት ፍጹማዊ እኩልነት አዳጋች መሆኑ እየታወቀ ለሴትና ወንድ እኩልነት ጥሪ እናደርጋለን። እስላም ግን ከተፈጥሯ ጋር በሚጣጣም ሁኔታ ተገቢ መብቷን በማክበር ፍትሐዊ አያያዝ ይደነግግላታል።

ኣደምሴት እስላም ውስጥ የተጎናጸፈችውን ያህል ክብርና ደረጃ በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ አልተጎናጸፈችም። ከፈላጋችሁ ከየትኛውም መለኮታዊም ሆነ ምድራዊ ሃይማኖት ጋር አነጻጽሩት።

ጆርጅሕጃብን፣ለሰላምታ መጨባበጥን፣ውርስናንና ሌሎቹንም በተመለከተ አሁንም ብዥታዎች አሉብኝ። ስለዚህም የበለጠ ግልጽ እንዲሆኑልኝ ጥረት አደርጋለሁ።

እስላምን በተመለከተ የሰጣችኋቸው መልሶች በአብዛኛው አዎንታዊ ከመሆኑ እውነታ በመነሳት ግልጽና ቀጥተኛ ጥያቄ አቀርብላችኋለሁእስላምን ተቀብላችሁ ከመስለም ምን አገዳችሁ? ጥልቀትና ተጨባጭነት ያለው ምላሽ በሁለት ቀናት ውስጥ ላኩልኝ።

ወዳጃችሁ ጆርጅ››

የቶምን የፌስቡክ ገጽ ከፈተ፣ይህ ነው የሚባል ነገር አላገኘም። ወደ ኣደም ፌስቡክ ገጽ ተዛወረ፤‹‹የመታደልን መንገድ በመፈለግ ላይ ከተሰማራው ወዳጄ የሚቀሰሙ ትምህርቶች 5›› በሚል ርእስ አዲስ መጣጥፍ ሰፍሮ አገኘ፦

‹‹ወዳጄ በመጨረሻዎቹ ደረጃዎች ላይ መሆኑን ካንድ ጊዜ በላይ ደጋግሜላችኋለሁ። የመታደሉ መንገድ እስላም መሆኑንና ያለ እስላም ለታላላቆቹ ጥያቄዎቹ ምላሽ የሚሰጥ አለመኖሩን በከፍተኛ ደረጃ አምኖ ተቀብሏል። ይሁን እንጅ ወደ ቅኑ መንገድ የመምራት ሥልጣን በአላህ እጅ ብቻ ነው። ባለቤቱ ትናንትና እስላምን ወድዳና በከፍተኛ ስሜት ውስጥ ሆና ታለቅስ ነበር፣ሰልማ ይሁን አይሁን ግን አላውቅም፤እያለቀሰች ነበር ወደ ቤቷ የተመለሰችው። አላህ ለዚህ ዓለምና ለወዳኛው ዓለም መታደል ያበቃት ይሆናል። ወዳጄን በተመለከተ ግን በአእምሮ ብስለቱና በግንዝባው ብቃት ብተማመንም ሙስሊሞችን እየፈራሁለት እስላምን በቅርበት ለማወቅ ወደ ግብጽ ሄዷል። የሚያሳዝነው ግን እዚያ ሆኖ በሙስሊሞች ስርቆት ተፈጽሞብኛል እያለ ነው። ይህን ፈተና ማለፍና ወደ እስላም መግባት የሚያስችል የልቦና ፍጹምነት አለው ብዬ ባምንም፣ስህተትና ችግሩ በእስላም በራሱ ምክንያት በመሆኑና በሙስሊሞቹ ምክንያት በመሆኑ መካከል ያለውን ልዩነት አልተረዳም። ትምህርቶቹን እንደሚከተለው ጠቅለል አድርጌ አቀርባለሁ

1. እስላም ምሉእ፣አጠቃላይና ከጉድለት የጠራ ሲሆን በተቃራኒው ግን ሙስሊሞች እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ስህተትና ጉድለት ይኖርባቸዋል።

2. ወደ እስላም ለመግባት የሚደረገው ውሳኔ ከፍተኛ ጀግንነትና ድፍረትን እንዲሁም ጥልቅ ግንዛቤን የሚጠይቅ ሲሆን፣ምናልባትም እነዚህ ነገሮች ለወዳጄ በእጅጉ ያስፈልጉታል።

3. ሰዎች በተሟላ ሁኔታ አሳማኝ ሆኖ እስኪገኙት ድረስ፣ወደ እስላም እንዲገቡና የመታደልን መንገድ እንዲይዙ ለማድረግ መጣደፍ አይገባም።

1.በሁሉም አንጻር የተሟላና በሁሉም አቅጣጫ አሳማኝ በመሆኑ፣በመታደል መንገድ ላይ የምንደብቀው ምንም ነገር የለም።

2.የመታደልን መንገድ ለማወቅ በአላህ የታደለ ሰው ሁሉ መንገዱን ለሌሎች በመልካም ሁኔታ ማብራራት ሲኖርበት ለዚያ የማብቃቱ (የህዳያ) ስልጣን ግን የአላህ ብቻ ይሆናል።

አላህ ልቡን ለመመራት ይከፍትለት ይሁን አይሁን በእርግጠኝነት ባላውቅም፣ለወዳጄ መልካሙን ሁሉ እመኝለታለሁ!

ስድስተኛውን ትምህርት ተጠባበቁ . .

ኣደም››

ኣደም ስለ ካትሪና የተናገረው በጣም ረብሾታል።
ካትሪና ሰልማለች ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል? ፈጽሞ ሊሆን አይችልም . . ምናልባት ኣደም በተሳሳተ መንገድ ተረድቷት ይሆናል።
እንዳውም ኣደም ለገጹ አንባቢዎች ካቶኪካዊት ሴት ወደ ሃይማኖቱ ማስገባት መቻሉን ዋሽቶ ለማሳየት እየጣረ ሊሆንም ይችላል። በትናንቱ የመጨረሻ ደብዳቤዋ እንደምትሰልም አልነገረችውም . . የኣደም መጣጥፍ መቼ ፖስት እንደተደረገ ሲመለከት ከሁለት ሰዓት በፊት መሆኑን ተረዳ። የ
ካትሪና ደብዳቤ ግን ትናንት ጧት የተጻፈ ነበር። ታድያ ትናንት ምሽት ሰለመች ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል? ከሆነስ ለምን አልነገረችውም?
የካትሪና የመጨረሻዎቹ ደብዳቤዎች፣ሁሉም ስለ እስላም አዎንታዊ አመለካከት የያዙ ብቻ ሳይሆኑ የስርቆት ክስተቱን በተመለከተ እስላምና ሙስሊሞችን ለያይተው የሚመለከቱ ናቸው። ታድያ ይህ ለመስለሟ ማስረጃ አይደለምን? ግን ደግሞ ካትሪና ሁሌም ለካቶሊካዊነት ተቆርቋሪ ናት፣ኢየሱስን ወደር በሌለው ሁኔታ ታፈቅራለች፣ለርሱም ብላ ነው ቤተክርስቲያን ለማገልገል ጉልበትና ጊዜዋን የምትሰዋው። ይህን ሁሉ እርግፍ አድርጋ መተው የሚቻል ነው?
ጆርጅ ሌሊቱን በከባድ የአእምሮ ጭንቀትና ግጭት ውስጥ አሳለፈ። አንዴ ባለቤቱ ያሻትን ማመን መብቷ መሆኑን ሲቀበል፣ሌላ ጊዜ ደግሞ በውስጡ በርሷ ላይ ሲቆጭ ይሰማዋል። እንደገና ደግሞ የመስለሟን ወሬ ያስተባብላል . . ለራሱ መስለም ቢፈልግ ለርሷ መንገር ይኖርበት ነበር ወይስ ያሳደረው ስሜት የወንድና ሴትን እኩልነት ያለመቀበል አንዱ መገለጫ ይሆን? . . ካንዴም ሁለቴ ሊደውልላት አሰበ፣ግን ራሱን ያዝ አደረገ።
እርሷ ራሷ መደወል ወይም ቢያንስ ኢሜይል መጻፍ ትችል አልነበረም? እናም ካትሪና እንዲህ ያለውን ከባድ ውሳኔ ገና ያልወሰነች ሳትሆን አልቀረችም . .

ግጭት . . (3)

ጆርጅ እየተጫጫነውና እየከባበደው ጧት አንድ ሰዓት ላይ ከእንቅልፉ ነቃ። በችኮላ ሻወር ወስዶ ለቁርስ ወደ ሆቴሉ ሬስቶራንት ሄደ። ከዚያም ወደ ሠራተኛ ኤጀንሲው አብረው ለመሄድ እንግዳ መቀበያው ውስጥ ቁጭ ብሎ የጀማልን መምጣት ጠበቀ።
ወደ ሠራተኛ ኤጀንሲው ኩባንያ ደርሰው ከሥራ አስኪያጁ ጋር ለመገናኘት ጠየቁ . .

- ከሚስተር ሙስጠፋ ጋር ትገናኛላችሁ አንዴ ቆዩኝ . .

- ጀማል፣የሥራ አስኪያጁ ስም ‹‹ሙስጠፋ›› ምን ማለት ነው?

- ከነብዩ ሙሐመድ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] ስሞች አንዱ ሲሆን፣በአላህ የተመረጠ ተመራጩ ማለት ነው፤ሙስሊሞች በዚህ ምክንያት ይጠሩበታል።

- ሙስሊም ነው ማለት ነዋ!

- በመሳረቱ እንደዚያ ነው።

ከአፍታ በኋላ ሚስተር ሙስጠፋ እየጠባቃቸው መሆኑን ጸሐፊው ነገራቸው . .

- እንኳን ደህና መጣችሁ።

- እንግዲያውስ ፍቀዱልኛና እኔ ልሂድ፣ጆርጅ ስድስት ሰዓት ላይ እመጣልሃለሁ።

- ከሚስተር ሙስጠፋ ጋር ምን ያህል ጊዜ እንደሚያስፈልገኝ አላውቅም።

- በኢሜይልህና በዝግጅታችን መሰረት ስምንት ሰዓት ላይ እንጨርሳለን ወይም ነገ በድጋሜ ትመጣለህ የሚል ግምት አለኝ።

- እንግዲያውስ ጀማል መልካም ፈቃድህ ከሆነ ስምንት ሰዓት ላይ እጠብቅሃለሁ።

- አንተ እንግዳችን ስለሆንክ ዛሬ ምሳ አብረን እንድንበላ እጠይቃለሁ።

- እናቴ ጆርጅን ዛሬ እኛ ዘንድ ምሳ እንድንበላ ይዠው እንድመጣ ጠይቃኛለች።

- በቃ እራት ከኔ ጋር ትበላለህ።

- ተስማምተናል፣ጀማል ስምንት ሰዓት ላይ እጠብቀሃለሁ።

- እኔ ደግሞ አንድ ሰዓት ላይ ወደ እራት እንድንሄድ ሆቴልህ ድረስ እመጣለሁ።

- ተስማምተናል፣በሉ ደህና ሁኑ።

ጀማል ወጣ፤ሙስጠፋ ፊቱን ወደ ጆርጅ አዞረ . .

- የቅርብ ወዳጆች ትመስላላችሁ።

- አዎ፣ከተዋወቅኩት ገና አጭር ጊዜ ቢሆንም ከሰውም ድንቅ ሰው ነው።

- ትውውቅህ የቅርብ ጊዜ እስከሆነ ድረስ ከነዚህ ሃይማኖተኛ እስላማውያን እንድትጠነቀቅ አሳስበሃለሁ።

- ሃይማኖተኛ እስላማዊ መሆኑን እንዴት አወቅክ?!

- ከአኳኋኑ በግልጽ ይታያል።

- ከምኑ ነው የምታስጠነቅቀኝ?

- እንዳይገድልህ ወይም እንዳይሰርቅህና የመሳሰለውን እንዳይፈጽምብህ ነው የማስጠነቅቅህ። ሊጠሉት የሚገባ ከሀዲ (ካፊር) ብቻ ሳትሆን መገደል ያለበት ሰው አድርገው ነው የሚመለከቱህ።

- ለምክርህ አመሰግናለሁ፤አንተ ከየትኛው የሙስሊሞች ጎራ ነህ?

- እኔ ሙስሊም ነኝ ግን ተራማጅና ዘመናዊ ነኝ፤ከፊል ሕይወቴን አሜሪካ ውስጥ ስለ አሳለፍኩ እስላማውያኑ ዘንድ የሌሉ አያሌ የሥልጣኔ ጉዳዮችን ተምሬአለሁ።

- እንዴት ያሉትን?

- ዴሞክራሲን፣የተለያዩ ሃሳቦች ማስተናገድ መቻልን፣የተለያየ ሃይኖት ካላቸው ጋር ተቻችሎ መኖርን፣ አንተ እንግሊዛዊ ነህና ከኔ ይበልጥ የምታውቃቸውን ሎሎች ነገሮችንም . .

- ይህ ያንተ ትህትና ነው፣ግን አነጋገርህ በጣም አስገርሞኛል፣እኛ ክርስቲያኖችም እኮ እናንተንም ኋላ ቀር ከሃዲዎች (ካፍር) አድርገን ነው የምንመለከታችሁ!

- ሙስጠፋ መጣፊያ አጣ፣ቀጠለና ‹‹እውነቱን ለመናገር አኛ ኋላ ቀሮች ነን፣በዚህ ረገድ ለኛ ያላችሁ አመለካከት ትክክለኛ ነው።›› አለው።

- ሊሆን ይችላል፣ለማንኛውም ሥራችንን እንጀምር።

- መልካም . . ሥራችንን እንጀምር፤ይሁንና ለሌሎች ሥልጣኔዎችና ባህሎች ክፍት አእምሮና ነጻ አመለካከት ካላቸው ሰዎች ጋር መስራት ግን ለአንተ ስኬታማነት ዋስትና ነው፣ከማትፈልገው ነገርም የሚያርቅህ ነው።

- ያለ ምንም ጥርጥር፣በተለይ ደግሞ አገሩንና ማህበረሰቡን የሚወድ ከሆነ!

- አመሰግናለሁ፤በኢሜይልህ መስፈርት መሰረት ምልምል ሠራተኞችን አዘጋጅቼልሃለሁ።

- መልካም፣ስንት ናቸው? አንተስ እንዴት ገመገምካቸው?

- ለመጀመሪያ ዙር ስምንት ሰዎች ናቸው፣አብዛኞቻቸው ለዓለም የተለያዩ ባህሎችና የአነዋነዋር ዘይቤዎች ክፍት አእምሮና ነጻ አመለካከት ያላቸው ናቸው።

- ጥሩ፣ሙያዊና ክህሎታዊ ብቃታቸውስ?

- መጥፎ አይደለም . . አንተ ራስህ አግኛቸው፤ቃለ መጠይቁን እንጀምር እንዴ?

- ይቻላል፣ከመግባታቸው በፊት ግን በቅደም ተከተላቸው መሰረት ሲቪዎቻቸውን ትሰጠኛለህ።

- ይኸውና፣በዝርዝሩ መሰረት ጸሀፊው እንዲያስገባቸው እነግረዋለሁ፤አሁን ወደ ሰውብሰባ ክፍሉ እንሂድ፣አንተን አድርስና ወደ ቢሮዬ ተመልሼ እጠብቀሃለሁ።

በሙስጠፋ የቀረቡለትን ስምንቱን እጩዎች ተራ በተራ ተቀብሎ አነጋገራቸው፣ለስምንት ሩብ ጉዳይ ላይ ሥራውን አጠናቀቀ . .

- አመሰግናለሁ፣ቃለ መጠየቁን ጨርሻለሁ።

- እንዴት አገኘሃቸው?

- ጥሩ ናቸው፣የነገውን ዙር ሳጠናቅቅ ነው የምወስነው። አሁን የጀማል መምጫ ነው፣ጨዋታችንን ማታ እራት ላይ ብንቀጥል ምን ይመስለሃል?

- መልካም ነው፣ምትወደውንና ምትደሰትበትን ሁሉ አዘጋጅቼልሃለሁ፤ጀማል እስኪደርስ ድረስ፣ ካነጋገርካቸው ስምንቱ ውስጥ ትኩረትህን የሳበ ወይም በሆነ ነገሩ ደስ ያለህ ሰው አለ?

- ትኩረቴን የሳበ ብዙ ነው፣ያስደነቀኝም ብዙ ነው።

- ዛሬ የሚያስደስትህን ሁሉ ታገኛለህ።

- እንዴት?

- እራት ላይ ይነገረሃል።

ጆርጅ ከኩባንያው ቢሮ ለቆ ሲወጣ ጀማል እየጠበቀው ነበር።
አብረው ወደ ጀማል ቤት አመሩ . .

- የዛሬ ውሎህ እንዴት ነበር?

- ምንም አይልም።

- ብዙም ያልረካህ ትመስላለህ!

- ፈጽሞ አላስደሰተኝም!

- ለምን?

- እኔ የምፈልገው ሙያተኛ ፕሮግራመሮችን ሲሆን እርሱ ያቀረበልኝ ግን ተራ የሰራተኞች ስብስብ ነበር።

- ምናልባት አንተ የፈለከውን አልተረዳ ይሆን?

- በሚገባ ተረድቷል፤ሥጋዊ ፍላጎቴን ብቻ ለማርካት የምፈልግ ሰው አድርጎኝ ነው የገመተው። ታውቃለህ ከቀረቡልኝ ስምንት እጩዎች መካከል አምስቱ ሴቶች ሲሆኑ ፕሮግራመሮች ሁለቱ ብቻ ናቸው። ወንዶች ሦስት ሲሆኑ ሁለቱ ብቻ የኮምፒውተር ሙተያተኞች ናቸው።

- ታድያ በምን መስፈርት ነው ሰዎቹን የመረጠልህ?

- በአብዛኛው በቁንጅና፣በሽቅርቅርነትና በመናፍቅነት መስፈርት ነው!

- ማለት የፈለከው ገብቶኛል፣ይቅርታ እጠይቅሃለሁ፣እኛ ግብጻውያን ግን እንደዚያ አይደለንም!

- ሊሆን ይችላል፣ካነጋገርኳቸው መካከል ልዩ ብቃት ያላቸው አንድ ወንድና አንድ ሴት ቢኖሩም፣ሁለተኛ ባላገኘው ደስ ባለኝ ነበር።

- ቀጠሮ የሰጠኸው እንደ መሆኑ ዛሬ አብረህ እራት ብላና ልዩ ብቃት አላቸው ያልካቸውን ለማግኘት ጠይቀው።

- ይህ የነገውን ቃለ መጠይቅ ከጨረስኩ በኋላ የማደርገው ይሆናል።

- ነገሮች ሁሌ በሚፈለገው መንገድ ላይሳኩ ይችላሉ፤ወደ ቤት ለመድረስ ጥቂት ነው የሚቀረን፤አሁን ወደ ሰፈሩ እንገባለን። ይቅርታ አድርግልኝና የምንኖረው በተራ ሰዎች ተራ ሰፈር ነው፣ባለ አምስት ወይም አራት ኮከብ ሆቴሎች የሉበትም።

- እኔ ይህንን ነው እምወደው፣አንተንና እናትህን ደጋግሜ አመሰገህናለሁ።

- እንደምታየው መንገዱ በጣም ጠባብ በመሆኑ ከዚህ በላይ በመኪና መግባት አንችልም፤በጣም ቅርብ ስለሆነ እስከ ቤቱ ድረስ ቀሪውን መንገድ በእግር እንጓዛለን።

እርጅና በሚስተዋልበት አሮጌ የመኖሪያ ሕንጻ ሦስተኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የጀማል አፓርታማ ደረሱ። ጀማል ለእንግዳ መቀበያነት ወደ ተዘጋጀችና በወግ ወደ ተያዘች ትንሽዬ ክፍል ጆርጅን ይዞ ገባ

. .

- ግባ እንኳን ደህና መጣህ፣ለአፍታ ፍቀድልኝ፣መጣሁ።

ጆርጅ በክፍሏ ውስጥ ያሉ ተራ የቤት እቃዎችን እያስተዋለ ቁጭ አለ። ተራና ቀለል ያሉ ነገሮችን የሚወድ ቢሆንም ወደ ሰፈሩ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ጀማል አፓርታማ ክፍል ድረስ ባየው በጣም ተገርሟል

እውን ይህ መኖሪያ ቤቱ ነው? ወይስ የሆነ ነገር አስቦብኝ ወደዚህ አምጥቶኝ ይሆን? ‹‹እነዚህ እስላማውያን ገዳዮች ሰራቂዎችና በቀለኝነት የተጠናወታቸው ናቸው . . ›› የሚለው የሙስጠፋ አባባል ትዝ አለው . . በእንግዳ ሀሳቡ ሳቀና በቦርሳው ስርቆት በወነጀለው ጊዜ ያሳየውን ታላቅ ስነ ምግባር አስታወሰ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ጀማል የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች የተደረደሩበትን ትልቅ ሳፋ ይዞ መጣ፤ሳፋውን ከጆርጅ ፊት አስቀመጠ . .

- ቆይቼብህ ከሆነ ይቅርታ፣በል ብስምላህ ጀምር።

- አመሰግናለሁ፣ብዙ ለፋህ።

- ምንም አልለፋሁም፣ምግቡን እኔ ሳልሆን ያዘጋጀችው እናቴ ናት። እርሷ ነች ለምሳ የጋበዘችህ፣ከአፍታ በኋላ መጥታ ሰላም ትለሃለች።

- እንግዳው ወደ ቤት ሲደርስ የጋባዡ አለመገኘት አስገራሚ ነው።

- ሴት በእስላም ውስጥ እናንተ ከምታስቡት በላይ ክቡር ነች፤የሚታዘዙላት ንግስት ነች፤የፈለገውን ቢሆን እናቴ የጠየቀችውን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ።

- የፈለገውን ቢሆን?!

- አዎ፣የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ።

ኡሙ ባስም መጥታ በሩ ላይ ቆመች፣ መሬት መሬቱን እያየች በግብጻዊ ቅላጼዋ ሠላምታ አቀረበች. .

- አሰላሙ ዐለይኩም የኔ ልጅ፣በመምጣትህ አክብረህናል አስደስተህናል፣ክብር ተሰምቶናል . . ባስም ሰላም ብሎህ አደራ ብሎናል . .

- ጆርጅ እናቴ እንኳን ደህና መጣህ ሰላም የኔ ልጅ፣በመምጣትህ አክብረህናል አስደስተህናል፣ክብር ተሰምቶናል . . ባስም ሰላም ብሎህ አደራ ብሎናል . . እያለችህ ነው።

- አመሰግናለሁ፣ለመናገር ቃላት ያጥሩኛል፣ለምን ከኛ ጋር አትሆንም . . እንብላ እንጂ።

- እናቴ የመጣችው እንኳን ደህና መጣህ ለማለትና አንተ ክብር እንግዳችን በመሆንህ ሁላችንም ልንታዘዝህ ዝጉጁ መሆናችንን ለማረጋገጥ ብቻ ነው።

- መስተንግዶአችሁና አቀባበላችሁ በጣም ከብዶኛል፤ይቅርታ አድርግልኝና ከኛ ጋር ለምን አልተቀመጠችም? ለምንስ አልጨበጠችኝም?

- እኛ ዘንድ ሴቶች የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ከወንዶች ጋር አይቀመጡም። በጋብቻ የማይገናኙ የቅርብ ዘመዶች ካልሆኑ በስተቀርም ወንዶችን አይጨብጡም።

- እንደነገርኩህ ዛሬ ለቃለ መጠይቁ አምስት ሴቶችን ያነጋገርኩ ሲሆን አራቱ ጨብጠውኛል፣አንደኛዋ ብቻ ልትጨብጠኝ ባለመፈለጓ በጣም ነው የተገረምኩት፤ሁሉም ግን አብሮኝ ቁጭ ብለዋል።

- ያልጨበጠችህ ምን ነበር ያለችህ?

- ወንዶችን እንደማትጨብጥ ገልጻ ይቅርታ ጠየቀችኝ።

- ያንተ አስያየትስ ምንድነው?

- ፍላጎቷን አከበርኩላት፤በተለይ ደግሞ ሁለቱ በአጨባበጣቸውም ሆነ በዓየኖቻቸውና በአካላዊ እንቅስቃሴአቸው ከጨዋ ስነ ምግባር ወጣ ያሉ ነበሩ።

- ወደ እንግሊዝ አገር ስሄድ ንግስቲቱን መጨበጥ ይፈቀድልኛል?

- ከዚህ ጋር ምን አገናኘው? በእርግጥ ንግስቲቱን ለመጨበጥ ሕጉ የሚፈቅድላቸው ለሰባት መደቦች ብቻ ነው።

- በኛ ሃይማኖት ውስጥ ሴት ልጅ የተከበረች ንግስት ናት ብየህ የለ?! እናም በትክክል ተለይተው ከተቀመጡ አስር መደቦች ውጭ ሌላ ወንድ እንዲጨብጣት እስላም አይፈቅድም። እነሱም አባት፣አያት፣ባል፣የባል አባት፣ልጅ፣ወንድም፣አጎት፣የወንድም ልጅና የእህት ልጅ ናቸው። እናንተ ንግስቲቱን ለማላቅና ለማክበር እንደምትከለክሉት ሁሉ እኛም ንግስታችንን ለማክበርና ከማይገቡ ነገሮች ልንጠብቃት ስንል እንከለክላለን።

- እህህ፣ የተከበረችና የታፈረች ንግስት! ታድያ ሴቶቹ ለምን ጨበጡኝ?

- ያሳዝናል፣ብዙ ሙስሊሞች በሃይማኖታቸው ጉዳ ላይ ችላ ባዮች ናቸው፤ሃይማኖቱ ግን ከነሱ ነጻ ነው።

- አሁን ገና ገባኝ፣ኣደም አንድም ጊዜ ካትሪናን ጨብጧት አያውቅም! ሴት በእስላም ውስጥ ስለምትይዘው ቦታ ብንወያይ ይከፋሃል?

- ስለ ንግስት ስትናገር እንዴት ይከፋዋል ብለህ ትጠብቃለህ?!

- እንግዳውስ ቀጥተኛ ጥያቄ ልጠይቅህ። የውርስ ድርሻዋን የወንድ ውርስ ድርሻ ግማሽ እየሰጣችኋት ንግስት ናት ትላላችሁ፤ንግስት ማድረጉን ትታችሁ ከወንድ ጋር እኩል አድርጓት።

- ለምትቀጥራቸው ሰራተኞች ሁሉ እኩል ደሞዝ ትከፍላቸዋለህ?

- ከርእሱ ለመውጣት የፈለክ ትመስላለህ!

- ፈጽሞ አልወጣሁም፣በርእሱ አንኳር ነጥብ ላይ እየተናገርኩ ነው።

- በእርግጥ እኩል አልከፍልም፣ለሥራ አስኪያጁና ለተላላከው እኩል ይከፈላል ብለህ ትጠብቃለህ?

- ለተላላኪው ከሥራ አስኪያጁ ያነሰ ስትከፍል ተላላኪውን በድለሃል ማለት ነው?

- አልበደልኩም፣ሁለቱንም በፍትሐዊ መንገድ ነው የማስተናግደው።

- እስላም በሴቶችና በወንዶች እንዲሁም በመላው የሰው ልጅ መካከል ፍትህን ለማስፈን ነው የመጣው እንጂ ሁሉንም በሁሉም ነገር እኩል ለማድረግ አይደለም። ለዚህ ነው ሴት በውርስ ድርሻ የወንድ ግማሽ ስታገኝ የምናየው። በተቃራኒው ደግሞ ሴቷን ከቀለብና ከሁሉም ወጪዎች ነጻ አድርጎ ኃላፊነቱን በወንዱ ላይ ይጥላል . . ይህም የፍትሀዊነት የተሟላ መገለጫ ነው።

- ለምን . . ባለቤትህ የቤታችሁን ግማሽ ወጭ አታዋጣም?

- የቤት ወጭ ሙሉ በሙሉ የወንዱ ግዴታና ኃላፊነት ነው። ንግሥቲቱ ከነክብሯ እያዘዘች ነው የምትኖረው።

ይቅርታ አድርግልኝማ . . ይህ ሴቲቱ እንዳትማር ወይም እንዳትሰራ አያደርጋትም?

- ማነው ያለው?! ልክ እንደ ወንዱ ሁሉ መማር ይኖርባታል፤አስፈላጊ ከሆነ መሥራትም መብቷ ነው . .

- የምታገኘው ደሞዝስ?

- የግል ንብረቷ ነው፣የቤት ወጭ ግዴታ የለባትም።

- እህህ፣እናም ከኢኮኖሚ አንጻር ከወንዶች ይልቅ ሴቶች አትራፊ ናቸው ማለት ነው።

- ከወንዶች በላይ በበለጠ ሳይሆን በፍትሐዊነት ነው፤ስነ ህይወታዊ ተፈጥሮዋ ከወንዱ እንደሚለይ ሁሉ፣የሚመለከቷት ድንጋጌዎችም በዚያው ልክ እንደ ባህሪዋና እንደ ሥራዋ ይለያያሉ።

- ስለ ፍትሐዊነት ውብ አገላለጽ ነው። በሌላ በኩል ግን ሕጃብ የተጣለባት ማህበራዊ በደል አይመስልህም?!

- መከበሪያና መታፈሪያዋ ነው እንጂ።

- በነዚህ ጨርቆች ተጠቅልላ ውበቷንና ሴትነቷን ስትሸፋፍን እንዴት ሆኖ?!

- ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት እናንተ ዘንድ የንግሥቶችና የልዕልቶች አለባበስ እንዴት ነበር?!

- ምን ለማለት ነው?!

- ጥያቄዬን መልስልኝ።

- ከነሙሉ መብታቸው ይኖሩ ነበር።

- አለባበሳቸው እንዴት ነበር?

- ዛሬ ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱትን ዓይነት ልብሶች ይለብሱ ነበር ማለትህ ነው?

- ያለ ምንም ጥርጥር አዎ፤በተጨማሪም ይህ የደናግልት ልብስ አይደለምን?

- ይሁንና እኛ ስናድግና ስንሻሻል የሴቶቻችን አለባበስም አብሮ ሊሻሻልና ሊለወጥ ችሏል።

- በመጀመሪያ የቤተክርስቲያን ሁኔታቸው - ለአባባሌ ይቅርታ- እየወረደ መጣ እንጂ እድገትና መሻሻል አላሳየም። አለባበሳቸው ግን አልተለወጠም፤የሴቶች አለባበስም እንዲሁ - አሁንም ይቅርታ - እየወረደና እየዘቀጠ መጣ እንጂ እድገት ወይም መሻሻል አላሳየም። የጾታዊ ትንኮሳ፣የዝሙት የውርጃና የሌሎችንም መዓቶች አኃዛዊ መረጃዎች አንብብ።

- እናንተ ዘንድም ያው ነው።

- ሰዎች ነንና እኛም እንሳሳታለን። ግን እኛ ዘንድ ያለው ከናንተው ጋር ሲነጻጸር የውቅያኖስ ጠብታ ያህል ነው። እሱም ቢሆን - አዝናለሁ - እናንተን ለመቅዳት ከናንተ የሚወሰድ ነው።

- እንዴት?

- አኃዛዊ መረጃዎችንና ጥናታዊ ዘገባዎችን ስለምወዳቸውና ስለሚያስደስቱኝ እንድጠቀማቸው ትፈቅድልኛለህ?

- አኃዛዊ መረጃ በጣም የተመጠነ ቋንቋ በመሆኑ ለኔ አሳማኝ ነውና መቀጠል ትችላለህ።

- ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአውሮፓና በአሜሪካ ካላገቡት ሴቶች መካከል 90% የሚሆኑት ዝሙትን ልቅ በሆነ ሁኔታ ወይም በየጊዜው ይፈጽማሉ። በአሜሪካ ከጋብቻ ውጭ የሚያረግዙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ 48% ይደርሳል። የአሜሪካ ኦፊሴላዊ ጥናቶችና የናሙና ዳሰሳዎች እንደሚያመለክቱት ከአጠቃላዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል 87.8% በሕይወታቸው ውስጥ ወሲብ ፈጽመው ያውቃሉ። ከነዚህ መካከል 22% የሚሆኑት አስራ ሦስት ዓመት ሳይሞላቸው ወሲብ ፈጽሟል። በስዊድን ደግሞ አዲስ ከሚወለዱ ሕጻናት መካከል 60% የሚሆኑት ያለ ምንም ትዳራዊ ትስስር ከጋብቻ ውጭ የሚወለዱ ናቸው።

ይበቃል . . የምዕራባዊውን ሕብረተሰባችንን ችግሮች ይህን ብቻ ሳይሆን የዚህን እጥፍ ድርብ አውቃለሁ። ይሁን እንጂ ይህ በመላው ዓለም የተንሰራፋ ችግር ነው፤እናንተም ብትሆኑ እንደኛው አይደላችሁም?

- እያዘንኩ ቅድም እንደነገርኩህ ከኛም እናንተን በመከተል ብዙዎች በዚህ መንገድ እየተጓዙ ነው። የሰው ልጅ ከሃይማኖት በራቀ ቁጥር እንዲህ ላለው ችግር ቅርብ ይሆናል፣ይሁን እንጂ በመካከላችን ያለው የቁጥር ልዩነት እጅግ በጣም ብዙ ነው።

- የናንተ የሃይማኖት መሪዎች እንደ ጳጳሳትና ደናግልት ይመነኩሳሉ አያገቡም ልትለኝ ትፈልጋለህ?

- ደጋግሜ ነግሬሃለሁ የሃይማኖት መሪና ካህን የሚባል ነገር በእስላም ሃይማኖት ውስጥ የለም። ነብዩ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] እንኳ አግብተዋል።

- ልክ ነህ ነብያችሁ ማግባቱን አንብቤ ተገርሜያለሁ! ይቅርታ፣ታድያ ባለቤትህ ዬት ናት? ባለትዳር ነህ አደለም?!

- ትምህርት ቤት ናት፤የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህርት ናት። የሥራ ሰዓቷ ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ሰዓት ነው፣ከጥቂት ጊዜ በኋላ ልትመጣ ትችላለች።

- እውነቱን ንገረኝና ሕጃብ እንድትለብስ አስገድደሃታል?!

- ስለ እውነት ፈጽሞ አላስገደድኩም።

- ታድያ የሌሎችን ሴቶች ሕጃብ እንዲለበሱ ስታስገድዱ ሴቶቻችሁን ሕጃብ እንዲለብሱ ለምን አታስገድዱም? ሃይማኖትን ለግለሰባዊ ጉዳዮች መጠቀም እንዴት አስጠሊ ነው!

- ራሷ በገዛ ምርጫዋ ሕጃብ ለባሽ በመሆኗ እኔ አላስገደድኳትም። ሃይማኖትን በግለሰባዊ ጉዳዮች ላይ በተሳሳተ መንገድ መጠቀምን በተመለከተ ካንተ ጋር እስማማለሁ ብቻ ሳይሆን ነብዩም [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] ይህን ከልክለዋል።

- አንተ ሳታስገድዳት በገዛ ፍላጎቷ ሕጃብ ትለብሳለች ነው የምትለኝ?

- በትክክል።

- ሕጃብ እንድትለብስ የሚያደርጋት ምንድነው?

- ሃይማኖቷና የፈጣሪዋ ትእዛዝ፤ከዚያም ራሷን ለመጠበቅ።

- ከምንድነው ራሷን የምትጠብቀው?

- ቅድም የጠቃቀስናቸው አኃዛዊ መረጃዎች ሰለባ ከመሆን! እህህ፣ተጨማሪ አኃዛዊ መረጃዎችንና ቁጥሮችን መስማት ካሻህ ብዙ አሉኝ።

- የለም . . ይበቁኛል እኔ ዘንድም በጣም ብዙ ይኖራሉ። ይቅርታ አድርግልኝና እንግሊዝ አገር ስለ ግብጻውያት ዘፋኞችና ተወዛዋዦች ብዙ እንሰማለን!!

- ልክ ነህ . . አዝናለሁ ከሃይማኖት እየራቅን በሄድን ቁጥር እናንተን እየቀዳንና እየተከተልን እንሄዳለን ብየሃለሁ።

- ማዘነህ ለምንድነው?

- ይቅርታ . . እናንተን ማስከፋት መፈለጌ አይደለም፤እናንተ ዘንድ ያለው የሴቶች ሁኔታ የደረሰበት የዝቅጠት ደረጃ ብዙዎቹ አስተዋይ ሰዎቻችሁን ጭምር ያሳሰበና ሕብረተሰቡ እየተጓዘበት ያለውን አደገኛ አቅጣጫ ቆም ብሎ ማጤን አስፈላጊ መሆኑን ጮኽ ብለው እንዲናገሩ እያደረገ ነው።

- አደገኛ አካሄዶች ብዙ ናቸው፤የትኛውን አደጋ ማለትህ ነው?!

- አንድ ሰው የሚፈልገውን ሁሉ ከጋብቻ ውጭ በቀላሉ የሚያገኝ ከሆነ ትዳር ለምን ይፈልጋል? ይህ ደግሞ ቤተሰባዊ ስርዓትን የሚነድና ወድቅ የሚያደርግ በመሆኑ የትኛውንም የዓለም ጠንካራ ሕብረተሰብ የሚያንኮታኩትና ከነአካቴው የሚያጠፋ አደጋ ነው።

- በይበልጥ አብራራው።

- በጣም ግልጽ ለመሆን በብዙዎቹ ምዕራባውያን ዘንድ አንድን ውሻ ተንከባክቦ ማሳደግ አንድን ልጅ ወልዶ ከማሳደግ ተመራጭ አይደለምን?! ሴት ጓደኛ ከሕጋዊ ሚስት ይልቅ ወጭዋ አነስተኛ፣በየጊዜው ለመቀያየርና በየዓይነቱ ለማማረጥም የቀለለ አይደለምን?!

- ይህ እንኳ የተዛባ ተፈጥሮ ባላቸው ዘንድ ብቻ ነው።

- እውነት ብለሃል፣ይህ አንዳንድ ሕብረተሰቦች የደረሱበት ሁኔታ ነው። በአንዳንድ ሕብረተሰቦች ውስጥ ልጅ የመውለድ ሁኔታ በያንዳንዷ ሴት ከአንድ ሕጻን ያነሰ መሆኑን ታውቅ የለም? እነዚህ ሕብረተሰቦች ቶሎም ሆነ ዘግይተው ከስመው መጥፋታቸው አይቀሬ ነው።

- እህህ፣ ለዚህ ነዋ ከአውሮፓም ጭምር በቁጥር የበላይ የሆናችሁት።

- ነብዩ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] {አፍቃሪና ወላድ የሆኑትን አግቡ} ይላሉ።

- በዚህ ዓይነቱ ዝርዝር ጉዳይ እንኳ ሳይቀር እስላም ጣልቃ ይገባል!

- እስላም እያንዳንዷን የሕይወት ዝርዝር ጉዳይ የሚያካትት አጠቃላይና የተሟላ የሕይወት መመሪያ ሃይማኖት ነው። ለዚህ ነው በእስላም ውስጥ ሕይወት ሚዘናዊ፣ነፍስን የሚያረካና አንዱ ጎን በሌላው ላይ ድንበር አልፎ የማያውክ አነዋነዋር የሆነው።

- የእስላም ዝርዝር ጉዳዮች አቤት ብዛታቸው! ለመሆኑ ይህ ድክመት እንጂ ጠንካራ ጎኑ ይመስለሃል?!

- እንዴት?!

- እነዚህን ረዥም ዝርዝሮች ተከታትሎ መፈጸም ለሰው ልጅ አድካሚ ነው። በሕይወት ላይ የተጣሉ ተጨማሪ ገደቦች ናቸው!

- እንደ እንግሊዝ ያለ ሕግ ያለበት አገር ወይስ ሕግ የሌለበትና ሥርዓተ አልበኝነት የነገሰበት አገር ይሻላል?

- ማለት የፈለከው ገብቶኛል፤ይሁን እንጂ ጥሩ ሕግ ነው ለፈጠራና ለጥረት ሰፊ ቦታ የሚሰጠው።

- በትክክል እስላምን እየገለጽክ ነው! ለፈጠራ ለምናብና ለእሳቤ በጣም ሰፊ የሆ አድማስ ከፍቶልናል። ለዚህም ነው ቁርኣን ውስጥ አድማሳትን፣ታሪክን፣ተፈጥሮንና ሌሎችንም እንድንመረምርና አዝንድናስተነትን የሚጠይቁ አንቀጾችን የምናገኘው።

- ሰዎች ከተመራመሩና ካስተነተኑ የሃይማኖታችሁን ድክመት እንዳያውቁ አትፈሩም?

- ይህ ሊሆን የሚችለው በምድራዊ ሰው ሰራሽ ሃይማኖቶችና በተዛቡና ተአማኒነታቸውን በከሰመ መለኮታዊ ሃይማኖቶች ዘንድ ብቻ የሚከሰት ነው። ሙስሊሞች ግን በተመራመሩና ባስተነተኑ ቁጥር እምነታቸው እርግጠኝነታቸውና ሃይማኖተኝነታቸው ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል። የሚያሳዝነው ግን መመራመርና ማስተንተን ባነሰ ቁጥር ሃይማኖኝነት የሚቀንስ መሆኑ ነው።

- በሃይማኖታችሁ ላይ ያላችሁ መተማመን አድናቆቴን ይስባል።

- አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እችላለሁ?

- ጠይቅ።

- እንዳትሰልም የሚያደርግህ ምንድነው?! እስላምን አሳማኝ ሆኖ አግኝተሃል የሚል ስሜት አለኝ!

ጆርጅ በጀማል ጥያቄ ትንሽ ተደናበረ . . ጣቶቹን በኃይል ጨበጥ አደረጋቸው . . ኣደም ስለ ካትሪና ማልቀስ ያሰፈረውና እርሱ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ሕሊናዊ ድፍረት እንደሚያስፈልገው የጻፈው ትዝ አለው። ጃኖለልካ በመጨረሻ ኢሜይሉ የጻፈለትንም አስታወሰ። በጥልቀት ወደራሱ ውስጣዊ ስሜት ተመለከተ . . እራሱ ለወዳጆቹ የላከላቸው ጥያቄም ይህ ራሱ መሆኑን አስታውሶ መልሱ ለምን እንደሚያስፈራው ራሱን ጠየቀ . . ድክመት ነው ወይስ ማመንታት? አለማወቅ ነው ወይስ አለመቸኮል?! ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ለጀማል መልስ ከመስጠቱ በፊት ለገዛ ራሱ መልስ መስጠት የግድ ነው . . ወደ ጀማል ፊቱን አዞረና . .

- አሁን መልስ እንዳልሰጥህ ትፈቅድልኛለህ?

- ውሳነው የራስህ ነው፣ይህን ያልኩህ መልካሙን ሁሉ ስለምወድልህ ብቻ ነው።

- አመሰግናለሁ . . በሁለት ወይም ሦስት ቀናት ውስጥ መልስ እሰጠሃለሁ።

- ለኔ መልስ መስጠት ብዙም አስፈላጊ አይደለም፣ዋናው ነገር ለገዛ ነፍስህና ለራስህ የሕሊና ጥሪ ምላሽ መስጠት ነው። የሚያሳዝነው ቁሳዊው ሕይወት ወደ ቁሳዊ እቃነት ስለቀየረን ካሰብክና ካስተነተንክ ትደክማለህ፤ለዚህ ነው የሰው ልጅ ከመታደል ርቆ የሚኖረው።

‹‹ለገዛ ነፍስህና ለራስህ የሕሊና ጥሪ ምላሽ መስጠት..
›› የሚለውን ሲሰማ ጆርጅ ተመቻችቶ ተቀመጠ፤መጀመሪያ ላይ አግኝቶት የነበረውን ሽማግሌ ቃል አስታወሰና
እንዲህ አለው፦

- በትክክል እኔን እየገለጽከኝ ነው።

- ይቅርታ እንድትከፋ ፍላጎት ኖሮኝ አይደለም፣ይህ ግን ከአላህ በሚያፈነግጡበት ጊዜ የመላው የሰው ልጆች ባህሪ ነው። ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል ፦ {ከግሣጼም የዞረ ሰው፣ለርሱ ጠባብ ኑሮ አልለው፤በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን።} [ጣሃ፡124] በተጨማሪም እንዲህ ብሏል ፦ {አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለእስላም ይከፍትለታል፤ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት እንደሚታገል ያደርገዋል። . . } [አል አንዓም፡125]

- የምትለው ነገር በጣም ከባድና ጭካኔ ነው!

- ይቅርታ . . ማክበድና መጨከን ፈልጌ ሳይሆን እውነታውን ብቻ መግለጼ ነው። ከአላህ ከመዞርና ከማዘንበል የበለጠ ጭካኔ የለም። ይቅርታ አሁን ብቻ ማለቴ ሳይሆን ሕይወትህን በሙሉ ማለቴ ነው!

- ምን ማለትህ ነው?

- ሰዎች በተለያዩ መንገዶችና ስልቶች ከራሳቸው ይሸሻሉ፤በጭፈራና በመጠጥ ከራሱ የሚሸሸግ አለ። ከፊል የመንፈስ ረሀባቸውን በሚያስታግስ ሃይማኖታዊ ፋሽን ብቻ የሚረኩ ሰዎችም ይኖራሉ። በደረቅ ፍልስፍና ውስጥ ራሳቸውን የሚደብቁም ይገኛሉ። ተጨባጩን እውነታ መጋፈጥ ተስኗቸው ወዳልታወቀ አቅጣጫ ከራሳቸው የሚሸሹም አሉ። ደግሜ ከልብ በመነጨ ፍቅር እለሃለሁ፦ ከዛሬው ሕይወትና ከነገው ዘላለማዊ ሕይወት መታደል የሚከለክልህ ነገር ምንድነው?

- በሁለት ወይም ሦስት ቀናት ውስጥ መልስ እሰጠሃለሁ ብየሃለሁ።

በመወያየት ላይ እያሉ የሚከፈት በር ድምጽ ሰሙ፤ጀማል ጆርጅን ይቅርታ ጠየቀ . .

- አንዴ ይቅርታ፣ባለቤቴ ዓእሻ መጥታለች።

- ከርሷም ጋር ጥቂት ብንነጋገር ትፈቅዳለህ?

- መጀመሪያ ላማክራትና ሀሳቧን ልስማ።

- ስለምኑ?

- ከወንዶች ጋር መነጋገር እንደማትወድ ስለማውቅ፣በማትፈልገው ነገር ለማስገደድ አልፈልግም፣አንዴ ይቅርታ።

ጆርጅን በመደመም ሁኔታ ውስጥ ትቶት ጀማል ክፍሉን ለቆ ወጣ። ዛሬ የሆነው ነገር በጽኑ አንቀጥቅጦታል፤ምን እንደሚያደርግ የማያውቅ ሆኖ ብኩንነት ተሰምቶታል . . ወደ ግብጽ ምን አመጣኝ? ብሎ ቀኑን ሙሉ ራሱን ሲጠይቅ ውሏል።
የራሴ ታላላቅ ጥያቄዎች እንኳ እንቅልፍ ይንሱኝ! ምንድነው የምፈልገው?
ለምንድነው የምኖረው?
ይህ
ሁሉ ድካም ስለምን? . . ወየው ጉዴ . .
በራሱ ጥያቄዎች ማእበል በመናጥ ላይ እያለ ጀማል ከባለቤቱ ጋር መጣ።
ቀና ብሎ ሲመለከታት ሕጃብ ለብሳለች፣ከፊቷ ተገልጦ የሚታየው በጣም አነስተኛው ክፍል ብቻ ነው . .

- ይኸውልህ ባለቤቴ እሷ ነች፤ምን መጠየቅ ትፈልጋለህ?

- መስለም እንደምትፈልግና ሴቶች በእስላም ውስጥ ስላላቸው ቦታ ጥያቄዎች እንዳሉህ ጀማል ነግሮኛል።

- ሴቶች በእስላም ውስጥ ስላላቸው ቦታ የማወቅ ፍላጎት ቢኖረኝም ፈጽሞ መስለም እፈልጋለሁ አላልኩም።

- መስለም የማትፈልግ ከሆነ ሴቶች በእስላም ውስጥ ስላላቸው ቦታ ለማወቅ ለምን ትፈልጋለህ?!

- እንዳው ለማወቅ ፈልጌ ነው።

- ሰውን የማይጠቅም ዕውቀት ዋጋ የለውም፤ባለቤቱን ከፍ የማያደርግ ዕውቀት ከንቱ ነው። ዕውቀት ወደ አላህ ፍራቻ ይወስዳል። ለዚህ ነው ኃያሉ አላህ እንዲህ ያለው ፦ { . . አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፤} [ፋጢር፡28]

- ፍላጎቴ ማወቅ ብቻ ነው ማለቴ ነው፤ጥሬ ዕውቀት እናንተ ዘንድ ነውርና ስህተት ነው እንዴ?!

- እኛ ዘንድ ለተግባር የማይበቃ ባዶ ዕውቀት ዋጋ ቢስ ነው። ከንቱነት፣ዓለማ የለሽነትና ግብ አልባነት የአእምሮም የሃይማኖትም በሽታ ስለመሆኑ በሚገባ ታውቁታላችሁ ብዬ አምናለሁ።

- እኛ ዘንድ ስትዪ ምን ማለትሽ ነው?!

- እኛ ሙስሊሞች ዘንድ ማለቴ ነው፤ተወኝና ወደምትፈልገው እንግባ፤መስለም ብትፈልግ እንጂ ጥያቄ እንደላቀረብክ እርግጠኛ ነኝ።

- እንዴት እርግጠኛ ሆንሽ?!

- እንደማላስከፋህ ተስፋ አደርጋለሁ፤ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል፦ {እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሮ በብዛት ይመኛሉ።} [አል ሒጅር፡2] የአላህን አንድነት የማያረጋግጥና ለርሱ ተመሪ የማይሆን ብልህ ሰው የቅዠት ዓይነቶች፣የተዛቡና ተአማኒነት የጎደላቸው ሃይማኖቶች አእምሮው ውስጥ እርስ በርስ የሚፋጩበት፣አእምሮው ግጭቶችን የሚያስተናግድ ሰው ብቻ ነሆን አለበት።

- ብልህ ስትዪ ምን ማለትሽ ነው?!

- ደካማ አስተሳሰብ ያለው ሰው በሕይወቱ ውስጥ የሚያጋጥሙ የሃይማኖት ተቃርኖችንና ግጭቶችን፣ውስጣዊ የህሊና ጥሪዎችንና ጥያቄዎችን ችላ ብሎ ራሱን ወደሚጠምድበት ተራ ጉዳዮች ዘሎ ማለፍ ይችላል። ነገር ግን . .

- ነገር ግን ምን?!

- ነገር ግን ብሩህ አእምሮ ያለህ ብልህ መሆንህን፣ጀማል የባስምን አስተውሎ የጠቀሰለትን ወንድሙን ዋቢ በማድረግ ነግሮኛል።

- አመሰግናለሁ . .

- ‹‹ሴቶች በእስላም ውስጥ ያላቸውን ቦታ›› ወደሚመለከተው ርእሰ ጉዳያችን እንግባና ከየት እንድንጀምር ትፈልጋለህ?

- ከፈለግሽበት ጀምሪ፤አስፈላጊ ሲሆን እኔ ጥያቄ አቀርባለሁ።

- እስላም ሲመጣ ዐረቦች ጨቅላ ሴት ሕጻናትን ሴት ሆነው በመወለዳቸው ብቻ ገድለው ይቀብሯቸው ነበር።

- የከፋ ኋላ ቀርነትና የጭካኔ ሥራ ነው!

- ልክ ነህ፤ይህ አስከፊ ሁኔታ ግን ዐረቦች ብቻ በተለይ የሚወቀሱበት አይደለም። በምዕራቡ ዓለምም ፈላስፎች በአንድ ከፍተኛ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ጉባኤ ይቀመጡ ነበር! በሚገርም ሁኔታ የመነጋገሪያ አጀንዳቸው ‹የሴት ነፍስ እንደ ወንድ ነፍስ ነው? ያላት የሰው ልጅ ነፍስ ነው ወይስ የእንስሳት ዓይነት ነፍስ ነው?!›› የሚል ነበር። የደረሱበት ማጠቃለያም ሴት ሰው ናት፣ያላት ነፍስና መንፈስ ግን በብዙ ደረጃዎች ከወንድ ያነሰ ነው የሚል ነበር። በተጨማሪም አንድ እንደ እቃ ሊሸጣትና ሊለውጣት ይችል ነበር። በሮማውያን ዘንድ የመፍታት የወለደችውን ልጅ የራሴ ነው ብሎ ያለመቀበል መብት የወንዱ ብቻ ነው። በግሪኮች ዘንድ ሴት ልጅ ፈጽሞ አትወርስም። በናንተ እንግሊዞች ዘንድም የሴት ልጅ እስከ ቅርቡ ዘመን ድረስ የራሷ ንብረት ባለቤት የመሆን መብት አልነበራትም።

- በጣም የሚያሳዝን ነው፣አስቀያሚ ታሪክ ነው!

- ሁሉም መለኮታዊ ሃይማኖቶች በመሰረቱ ለሴቶች ፍትህ ይዘው የመጡ ቢሆንም፣በሚያሳዝን ሁኔታ አይሁዳዊነት ይህን አዛብቶታል። የተዛባውና የተጣመመው መጽሐፋቸው በወሲባዊ ምናቦችና በሴቶች ላይ በሚፈጸም መራራ ግፍ የተሞላ ነው።

- በዚህ ጉዳይ ላይ ከሌቪ ብዙ ሰምቻለሁ፤እኔም ብዙ አንብቤአለሁ።

- ሌቪ ማናት?!

- በጣም ድንቅ የሆነች ጨዋ አይሁዳዊት ሴት ነች።

- በእስላም መታደልን መከበርንና መታፈርን እንዲታገኝ እመኝላታለሁ።

- አይመስለኝም፣ለማንኛውም ቀጥይ።

- የልቦች መክፈቻ ቁልፍ ያለው በአላህ እጅ ነው። እንቀጥልና ክርስትናም እንዲሁ በሴቶች ላይ ፍትሕ አዛብቷል፣በሚያሳዝን ሁኔታም ሴቶችን በሚያንቋሽሹ ምንባቦች የተሞላ ሆኗል።

- ጥሩ የሀሳብ ፍሰት ነው።

- ከዚህ በኋላ እስላም መጣና በየትኛውም ሃይማኖት ያላገኘችውን ክብርና ፍትሐዊ አያያዝ አጎናጸፋት። እስላም ሳይዛባና ሳይከለስ ሲተላለፍ በነበረበት ሁኔታ ያለና የሚኖር ብቸኛው ሃይማኖት ነው፤ለጥበቃውም ከኃያሉ አላህ ዋስትና ተስጥቶታል።

- እስላም ያልተዛባና ያልተበረዘ ስለ መሆኑ በሚገባ አውቃለሁ፤አንዳንድ ጥያቄዎች ቢኖሩኝም መጀመሪያ የራስሽን እንድትቋጭው እፈልጋለሁ።

- ሴት በእስላም ውስጥ ያገኘችውን ከበሬታ መቼም ቢሆን አግኝታ አታውቅም። አውሮፓ ከሙስሊሞች ጋር በነበራት ንክኪ ስለ ሴት ልጅ ከበሬታ አንዳንድ ነገሮችን፣ዕውቀትንና ፍትሕ ማስፈን ተምራለች። ይህ ሁሉ ግን ከተዛቡና ከተከለሱ መጽሐፎቻቸውና ከቤተክርስቲያን ትምህርቶች ጋር ስለ ተላተመባቸው በቤተክርስቲያን ላይ አመጹ። የሚያሳዝነው ሳይሰልሙ ቀሩና ለሴት ከበሬታ የሚሰጥ ሥርዓት ለማግኘት ሲፈትሹ ሰብአዊ አእምሯቸው ወደ ጾታ እኩልነት መራቸው።

- ታድያ ሰብአዊ አእምሮ ከሃይማኖቶች ደረጃ አልፎ መጥቋል ማለት ነዋ?!

- በእርግጥ ባህሪዋን ተፈጥሯንና ሚናዋን ለውጠው ከወንዱ ተፈጥሯዊ ባህሪና ሚና ጋር ማጣጣም አዳጋች ሆነባቸው። በመሆኑም ከራሷ ተፈጥሯዊ ባህሪና ሚና ጋር የወንዱንም ሥራ እንድትሠራ ወሰኑባት! የሚገርመው ግን ከራሷ ሥራ ጋር የወንዶችን ሥራ የምትሠራው ወንዱ ከሚያገኘው ደሞዝ ግማሽ ወይም ሩቡ ብቻ እየተከፈላት መሆኑ ነው! ከተፈጥሯና ከሚናዋ ውጭ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በማትችለው ነገር ላይ በማሰመራት ብቻ አልተወሰኑም፤ወደ ርካሽ ሸቀጥነት ለውጧት ዋስትና ያላት የተከበረች ሕጋዊ ሚስት ከመሆን ጊዜያዊ የወሲብ መገልገያ ‹የፍቅር ጓደኛ› እንድትሆን ፈረዱባት። የጾታ እኩልነትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ይህን አስከፊ ሁኔታ ለመለወጥ ዘመቻ አድርገው ብዙም አልተሳካላቸውም።

- የምትናገሪው ሁሉንም ምዕራብና ሁሉንም ሁኔታ አይወክልም።

- ልክ ነህ፣ግን ብዙዎቹን ይወክላል። ወደዚህ የከፋ ደረጃ ገና ያልወረዱ ይኖራሉ። አደጋው ግን በእኩልነት፣በነጻነትና ከወንዶች የበላይነት በመገላገል ስም የሴት ልጅ ወደ ከፋ ልቅነትና ዋልጌነት እየተገፋች፣ሰብእናዋ ተገፎ ወደ እንስሳነት ደረጃ እንዲትዘቅጥ እየተደረገ መሆኑ ነው።

- ምን እያልሽ ነው?!

- አነጋገሬ ትንሽ ሻካራ ሆኖ ወይም እናንተን የሚያንቋሽሽ አድርገህ ተረድተህ ከሆነ ይቅርታ። ማለት የፈለኩት በእኩልነት ስም የሴት ልጅ የወንዶች መጫወቻ፣ማሳሳቻና ማባበያ አሻንጉሊት ወይም የንግድ መስታውቂያ ሆናለች። ይህ ባይሆን የወሲብ ቲቪ ቻናሎችን፣ፊልሞችን፣መጽሔቶችንና ሕጋዊ የወሲብ ንግድን . . አንዴት ልንተረጉማቸው፣ምን ልንላቸው ነው?

- ለዚህ ውብ ፍጡር የሚቸር አንድ ዓይነት የአድናቆት መግለጫ ነው ማለት ይቻላል!

- እናም ከወንዶች የተለየ ውብ ፍጠር መሆመኗን አምነህ ተቀብለሃል፣ስለዚህም ከወንዱ ጋር አንድና እኩል ናቸው ማለቱ ለርሷም ለርሱም በደል ማለት ነው። እኔ ግን በነዚህ ህብረተሰቦች ውስጥ የሚገኘው ወንድ ቁሳዊ መብቶቿን ከነጠቃት በኋላ፣ራሱን አሳርፎ የርሱንና የራሷንም ሥራ አጣምራ እንድትሠራ በማድረግ ሰብአዊ ክብሯን ገፎ ወደ ተራ የመደሰቻና የመዝናኛ ሸቀጥነት ለውጧታል ብዬ ነው የምተረጉመው። አለዚያማ በብዙዎቹ አገሮች ውስጥ በመጽሔቶች የፊት ሽፋን ላይ ልክ የቤት እቃ ወይም መኪና ወይም ሌላ ማንኛውም የሸቀጥ ማስታውቂያ እንደሚወጣው ሁሉ የሴት ልጅ እርቃነ ገላዋን ሆና መቅረቧ ምን ሊባል ይችላል?!

- በእርግጥ ይህ በጣም የሚያስከፋ ነገር ነው፣በትክክል ግን ማህበረሰባችንን አይወክልም።

- እነዚህ ነገሮች ቢያንስ ሕጋዊ ከለላ የሚሰጣቸውና በተቀነባበረ መንገድ የሚካሄዱ ሲሆኑ፣በሌላ በኩል ግን የሚፈልጉ ሰዎች ሕጃብ እንዳይለብሱና ገላቸውን እንዳይሸፍኑ በሕግና በተደራጀ መልክ ይከለከላሉ። ሥርዓቱ ሌላዋን ሴት ለሽያጭና ለግብይት የምትቀርብ ሸቀጥ እንዲትሆን ሲፈቅድ ሙስሊሟ ሴት ግን ሕጃብ እንዲትለብስ ግን አይፈቅድም።

- በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች የሚፈጽሙ የመብት ጥሰቶችን አወግዛለሁ፣አልቀበልም።

- እንግዳውስ በናንተው መስፈርት መሰረት አንተ አሸባሪ ነህ ማለት ነው። . . አበዛሁባችሁ ይቅርታ፤ባለቤቴ ባጠይቀኝና ለመስለምህ ምናልባት ምክንያት ብሆንስ ብዬ ባላስብ ኖሮ አልመጣም ነበር።

- አንዴ በፍጥነት፣ለሌሎች ያቀረብኳቸው ጥያቄዎች አሉኝ፣ምላሻቸውን ከሴት ማግኘት እፈልጋለሁ።

- እሽ፣ጠይቅ።

- አንቺ ከኛ ዘንድ ወደ እናንተ ከመጡና ለእድገታችሁ አጋዥ ከሆኑ ዋነኛ ዘመናዊ ዕውቀቶች አንዱ የሆነው የፊዚክስ ባለሙያ ነሽ። ከዚሁ ጋር ሕጃብ ትለብሽያለሽና ለመልበስ ተገደሽ ነው?! ወይስ እኛ ዘንድ እንዳለው ዓይነት የደናግልት አለባበስ ራስን ለመጠበቅ ሳይሆን ባህላዊ አለባበስ በመሆኑ ነው?! ወይስ የምትኖሩበት ሕብረተሰብ ሥጋዊ ፍላጎቱ ጣርያ የነካ በመሆኑ ለጾታዊ ትንኮሳና ለመሳሰሉ ችግሮች ላለመጋለጥ የግድ መልበስ ስላለብሽ ነው የለበስሽው?!

- እህህ፣አንደኛ ነገር ዕውቀት የመላው የሰው ልጅ ውርስ ነው። እንደ ዛሬ ከናንተ ዘንድ ዕውቀት ወደኛ ከመምጣቱ አስቀድሞ እናንተ በድቅድቅ የማይምነት ጨለማ ውስጥ በነበራችሁበት ዘመን የተለያዩ ዕውቀቶች ከኛ ዘንድ ወደ እናንተ መጥተዋል። ጾታዊ ትንኮሳ በከፊል እርቃነ ገላ በመሄድና የተወጣጠሩና ገላን የሚያስነብቡ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶች ጋር በቀጥታ ግንኙነት እዳለው ታውቃለህ። ይህን የሚደግፉ አኃዛዊ መረጃዎችን ከፈለክ መነጋገር እንችላለን። እኔን በሚመለከት ግን ሕጃብ የምለብሰው በሃይማኖታዊ ትእዛዝነቱና ለዛሬውም ሆነ ለወዳኛው ሕይወቴ መታደል መሆኑን በማወቄ ነው። ለዛሬ ሕይወቴ እርካታና እርጋታ ሲሆን ለወዳኛው ሕይወቴ ደግሞ የቸሩ አላህ ችሮታና ምህረቱን ማስገኛ ነው።

- ‹‹በዛሬው ሕይወትና በወዳኛው ሕይወት መታደል›› የሚለውን ሁሌ ትደጋግማላችሁ።

- ልክ ነህ . . በተግባር የሞከረው ሰው እንጂ ሌላው የማያውቀው መታደል በመሆኑ ነው።

- ሊሆን ይችላል፣ግን ደግሞ ግልጽ ሁኚና ነብያችሁ እንዳደረገው ሁሉ ጀማል በአንቺ ላይ ሌላ ሚስት ቢያገባ ደስተኛ ትሆኛለሽ?!

ዓእሻ ከጎኗ በዝምታ ወደ ቆመው ጀማል ተመለከተችና ቀጠለች . .

- ጀማል ይህን ያደርጋል ብዬ አላስብም፣በኔ ላይ ባያገባ ምኞቴ ነው።

- ነብያችሁ ግን ብዙ ሚስቶች አግብቷል!

- ልክ ነህ፣ነብዩ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] ብዙ አግብተዋል፣ከእመ ምእመናን ሚስቶቻቸው መካከል አንደኛዋ ስማቸው እንደኔው ዓእሻ ነው።

- ታድያ ጀማል የነብዩን አርአያ በመከተል በአንቺ ላይ እንዲያገባ የማትፈልጊው ለምንድነው?!

- እስላም ሴት እንዳልሆን አልጠየቀኝም፣መቅናት መብቴ ነው። እስላም ፍላጎቴንና የምወደውን ነገር መግለጽ የማልችል ደካማ እንድሆንም አልጠየቀኝም። ከአንድ በላይ ማግባት ቅምጥ ፍቅረኞችን ከመያዝ የተሻለ መሆኑን ግን በእርግጠኝነት አውቃለሁ።

- በጥቅሉ ሲታይ ግን ከሁሉም ተመራጩ ከአንድ በላይ አለማግባቱ ነው . .

- ከአንድ በላይ ማግባት በአንዳንድ ወንዶች ተፈጥሮ ምክንያት የሰው ልጆች ባህሪ አንዱ ገጽታ ነው የሚል እምነት አለኝ። በመሆኑም ከአንድ በላይ ማግባት በእስላም ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ የሚገኝ ነው። ልዩነቱ በቀደሙት ሃይማኖቶች ውስጥ በቁጥር ያልተገደበ ልቅ መሆኑ ሲሆን እንደምታውቀው ነብዩ ሱለይማን አንድ ሺ፣ኣደም አስራ ሦስት፣ነብዩ ዳውድ ስልሳ ዘጠኝ አግብተዋል። እስላም ውስጥ ግን በአራት ብቻ የተገደበ ነው።

- በአሁኑ ዘመን ግን አንቀበለውም፣አብዛኞቹ ስርዓቶችም በሕግ ይከለክላሉ።

- መጽሐፍ ቅዱሳችሁ በዚህ የተሞላ ነው፤አንዳንዶቹ የናንተ ቀሳውስት ይህን ማብራራት ሲያቅታቸው አንዴ ይህ የሰው ልጆች ስህተት ነው በማለት ነብዮቹን ይወቅሳሉ። ሌሎቹ ደግሞ በአንድ የታሪክ ወቅት ላይ ጦርነቶች የበረቱ ስለነበር የሴቶች ቁጥር ከወንዶች የበዛ ስለነበረ ነው ይላሉ። በዚህም ዛሬ ያለው የጦርነት ብዛትና ክፋት ከቀድሞው ዘመን የባሰ መሆኑን በመርሳት ከእውነታ ጋር ይጋጫሉ።

- ዋናው ነገር ከአንድ በላይ ማግባትን ለመከልከል ሲባል ሃይማኖታችንን፣ሥርዓቶቻችንን እና ሕጎቻችንን ያሻሻልናቸው መሆኑ ነው።

- {ሃይማኖታችንን አሻሽለናል›› መባሉ አስገራሚ ነው። እውነተኛና የተሟላው ሃይማኖት መሻሻልም ሆነ ለውጥ የማይቀበል ለሁሉም ጊዜና ስፍራ ተስማሚና ተፈጻሚ የሚሆን ሃይማኖት ነው። ለዚህ ነው ኃያሉ አላህ እስላምን አስመልክቶ እንዲህ ያለው፦ {ዛሬ ሃማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም እስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፤} [አል ማኢዳህ፡3] የተሟላና ማሻሻያ የማይቀበል ምሉእ በመሆኑ እኛ ሃይማኖታችንን አናሻሽልም።

- ጨቋኙን ከአንድ በላይ ማግባት ለመከልከል ስንል እኛ ግን አድርገነዋል።

- ልክ ነው፣በአብዛኞቹ የአውሮፓና የአሜሪካ አገሮች ከአንድ በላይ ማግባትን በግልጽና በይፋ የከለከላችሁ ሲሆን ቅምጥ ፍቅረኞችን በየዓይነቱ መያዝን ግን በግልጽና በይፋ ፈቅዳችኋል።

- ቁም ነገሩ ካንድ በላይ ማግባትን መከልከላችን ነው።

- የሰውን ልጅ ተፈጥሮና ማህበራዊ ሕይወት ከአንድ ሚስት በላይ ከሚያስፈልጋቸው አንዳንድ ወንዶች ፍላጎት ጋር ለማጣጣም ስትሉ ብዙ የፍቅር ጓደኞችን መያዝ ፈቅዳችኋል። ይበልጥ አስከፊው ደግሞ በአንዳንድ አገሮች ከብዙ ሚስቶች ይልቅ ብዙ ባሎችን ማግባት የሚፈቀድ መሆኑ ነው። በቡድን ሆነው አንዲት ሴት ማግባትም ሲፈቀድ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ግን አይፈቀድም። በመሆኑም ለአንዲት ሴት ባሏ በርካታ ቅምጥ ወዳጆችን ከሚይዝ ወይም በአስቀያሚው የቡድን ጋብቻ ላይ ከሚሳተፍ በሕጋዊ መንገድ ተጨማሪ ሚስት ማግባቱ ክብሯን ያስጠብቃል።

 

- መልካም፣የተማርሽውና በማስተማር ላይ ያለሽው ዘመናዊ ዕውቀት ግን ምናልባት ከሃይማኖታችሁ ትምህርቶች ጋር ብዙ ሊጋጭ ይችላል!

- ሳይንስ ከሃይማኖታችን ጋር ሊጋጭ! አንተ ሃይማኖታችንን አታውቅም ወይም ስለ ሳይንስ የምታውቀው ነገር የለም ማለት ነው። ለማንኛውም በሳይንስና በሃይማኖት መካከል ስላለው ግንኙነት ጀማል ከኔ ይበልጥ ያውቃል፤በሴቶች ጉዳይ ላይ እንዳናግርህ ነበር የጠየቀኝ፤ባልጠየቅ ኖሮና ሃይማኖትን ማገልገል ነው ብሎ በያሳምነኝ መናገር ፍላጎቴ አልነበረም። መልካም ፈቃዳችሁ ከሆነ አሁን ልሂድና ልጄን ላስጠና።

ዓእሻ ወጥታ ሄደች . . በመደመም ስሜት ፈገግ እያለ ጆርጅ ፊቱን ወደ ጀማል አዞረ . .

- በባለቤትህ እንኳን ደስ አለህ እለሃለሁ፣ግና ወንድ እንጂ ሴት መሆን አይገባትም ነበር።

- እህህ።

- ምነው ምን አሳቀህ?!

- እንግዳውስ ወንድ እንደ ሴት አለመሆኑን ታረጋግጣለህ ማለት ነው። ታድያ ለምንድነው ለጾታ እኩልነት ጥሪ የምታደርገው?! ከሚስት በላይ ለባል ታዛዥና ርህሩህ ማን አለና! ሃይማኖተኛ በመሆኗ ለባሏ ታዛዥ እንድትሆን ከነብዩ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] የተላለፈውን ትእዛዝ ታከብራለች።

- ዳግም ወደ ማበላለጡ ተመለስን፤ነብያችሁ አንተ ለርሷ ደግ እንድትሆን ለምን አላዘዘህም?

- በሚገባ አዘውናል፤[የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] እንዲህም ብለዋል፦ {በላጫችሁ ለቤተሰቡ ከሌላው ይበልጥ ጥሩ የሆነ ሰው ነው፣እኔ ከሁላችሁም ይበልጥ ለቤተሰቤ ጥሩ ነኝ።} በውይይትህ በጣም ደስተኛ ነኝ፣አንዴ ሄጄ ዐስር እንድሰግድ ግን ፍቀድልኝ።

- አሁን አስር ሰዓት ተኩል ነው፤የሚመች ከሆነ አብረን እንውጣና አንተ እስክትሰግድ ድረስ እኔ ለአንድ ሰዓት ያህል ካይሮ ውስጥ ዞር ዞር እልና ከዚያ ወደ ሙስጠፋ ትወስደኛለህ፣ለምን እንደሆነ እንጃ ለእራት ቀጥሮኛል።

ግጭት . . (4)

ጀማል ሰግዶ እስኪወጣ ድረስ ጆርጅ መኪና ውስጥ ቆየ፤ሶላቱ ካበቃ በኋላ ከመስጊድ የሚወጡ ሰዎችን ፊት ማስተዋል ያዘ፤አውሮፓዊ ገጽታ ያለው ሰው ተመለከተና ምልክት ሰጥቶት ሄዶ ሰላምታ አለው . . በተሰባበረ እንግሊዝኛ መለሰለት . .

- ሰላም፣ እኔ ዊልያም እባላለሁ፣ከየት አገር ነህ?

- ጆርጅ እባላለሁ፣ከእንግሊዝ ነኝ።

- እኔ ደግሞ ፒተር እባላለሁ፣ከጀርመን ነኝ።

- ከሙስሊሞቹ ጋር ስትሰግድ ነበር!

- ልክ ነህ ጀርመናዊ ሙስሊም ነኝ።

- ጀርመናዊ ወይስ ጀርመን የምትኖር ግብጻዊ?

- አውሮፓ ከሚገኙ ሙስሊሞች ግማሾቹ ነባር የአገሬው ሰዎች ሲሆኑ እኔም ከነርሱ አንዱ ነኝ። በጀርመን የሙስሊሞች ቁጥር ከአራት ሚሊዮን የሚበልጥ ሲሆን ከሕዝቡ 5% ይሆናሉ።

- አውቃለሁ . . እኛ ዘንድ በአገረ እንግሊዝ ቁጥራቸው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሲሆን ከጠቅላላው ሕዝብ 3% ይሆናሉ። የኔ ጥያቄ ግን ክርስቲያን ነበርክ ወይ? ነው።

- አባቴና እናቴ ክርስቲያኖች ነበሩ፤እኔ ግን ኤቲስት ነበርኩ፤አላህ ይመስገን አሁን ሰልሜ መታደልን ተጎናጽፌያለሁ። እዚህ የተገኘሁት እስላምን ለማጥናት ነው።

- ወደ እስላም እንድትገባ ያደረገህ ምንድነው?!

- ብዙ ጊዜ የሚቀርብልኝ ጥያቄ ነው። ወደ እስላም የገፋፋኝን ነገር ጠቅለል ባለ መልኩ የሦስት ቃላት ፍለጋ ነው ማለት እችላለሁ፤እነሱም ፦ እውነታ፣መታደል እና ፍትሕ ናቸው።

- እስላም ውስጥ አገኘኻቸው?! እንዴትስ ማግኘት ቻልክ?

- አዎ አግኝቻለሁ፤ዝርዝሩን ማወቅ ከፈለክ በኋላ ብትጎበኘኝ ደስታዬ ነው፤አሁን ከአንድ ወዳጄ ጋር ቀጠሮ ሳለለብኝ ይቅርታ አድርግልኝ። እንካ ይህ ሙሉ መረጃዬን የያዘ የአድራሻ ካርዴ ነው።

- አመሰግናለሁ፤በማስተጓጎሌ ይቅርታ።

ጆርጅ ወደ መኪናው ሲመለስ ጀማል እየጠበቀው ነበር . .

- መቼ ተመለስክ?

- ከሰውየው ጋር ስትነጋገር አይቸሃለሁ፣ላቋርጥ አልፈለኩም። አሁን አስራ አንድ ተኩል ነው፣ለሙስጠፋ ቀጠሮ ምን ያህል ቀረህ?

- አንድ ሰዓት ያህል ይቀራል፤እውነቱን ለመናገር ግን በጣም ስለ ደከመኝ ወደ ሆቴል ሄጄ አረፍ ብል ደስ ባለኝ ነበር፤ዳሩ ግን በማላውቀው ምክንያት እንድገኝለት በጣም ጉጉ ስለነበር ቀጠሮ ሰጥቼዋለሁ፣ስለዚህም ማፍረስ አልፈልግም።

- መልካም ነው፤ቁርኣንና ነብዩም [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] ቀጠሮ እንድናከብር አጥብቀው አሳስበዋል። ማን ያውቃል ለበጎ ነገር ሊሆን ይችላልና መሄድህ ተገቢ ነው። እስከዚያ ድረስ ግን በቀሪው አንድ ሰዓት ውስጥ በጀልባ አባይ ወንዝ ላይ ላንሸራሽርህ፣የቀጠሮህ ቦታም ለአባይ ቅርብ ነው።

- ድንቅ ሀሳብ ነው።

ወደ አባይ ወንዝ አመሩ፤ለአንድ ሰዓት ጀልባ ተከራዩና ለጆርጅ ትልቅ የእርካታና የእፎይታ ስሜት የሰጠ ረጋ ያለ አዝናኝና አስደሳች ሽርሽር አደረጉ። በጉዞው ላይ አእምሮው ውስጥ የሚጉላሉ የመረጃ ክምችቶች በድንገት እየተቀነባበሩ ፈርጅ ፈርጃቸውን ሲይዙ ተሰማው፤ከዚያም ወደ ሙስጠፋ ቀጠሮ ቦታ አቀኑ . .

- አመሰግናለሁ፣ወቅቱን የጠበቀ ድንቅ ጉዞ ነበር።

- እንሻአላህ ትንሽ እረፍት አግኝተሃል ብዬ አስባለሁ።

- ልክ ነህ፣ግን ትንሽ ዘና ባልኩ ቁጥር የትላልቆቹ ጥያቄዎቼ ጫና አሁንም እረፍት ይነሳኛል።

- የትኞቹ ጥያቄዎች?

- አንድ ጥያቄ እንድጠይቅህ ትፈቅድልኛለህ?

- ጠይቅ።

- ለምን ዓለማ ተፈጠርኩ ብለህ ራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ?

- አዎ . . ብዙ ጊዜ እላለሁ . .

- ምን ብለህ ነው ለራስህ መልስ የምትሰጠው? ወይም ከጥያቄው እንዴት ነው የምትሸሸው?

- ቁልጭ ያለ ምላሽ እያለኝ ለምን እሸሻለሁ?!

- መልሱ ምንድነው?

- ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል፦ {ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።} [አል ዛሪያት፡56]

- ለእግዚአብሔር ለመስገድና ለመጾም ብቻ ነው የተፈጠርኩት ልትለኝ ነው?!

- አይደለም . . በተሟላ አጠቃላይ ጽንሐሳቡና ግንዛቤው ለአምልኮት ነው የተፈጠርከው፤ጸሎትና ጾም ከአጠቃላዩ አምልኮ (ዕባዳ) አበይት ክፍሎች አንዱ አካል ብቻ ናቸው።

- እንዴት?

- አምልኮ የሕይወታችንን አጠቃላይ ፈርጆች ሁሉ የሚያካትት እንጂ በተለየ ቀን ወይም ቦታ ወይም በተወሰነ እድሜ የሚገደብ አይደለም። ከዚህ አልፎ ነብያችን [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር በመገናኘቱና በመደሰቱ እንኳ ከአላህ ምንዳ እንደሚያገኝ አስተምረውናል።

- እንዴት?

- ነብዩ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] ይህን እንዲህ ሲሉ ነው ያብራሩት ፦ {ባልተፈቀደለት ሐራም ሁኔታ (በዝሙት) ፈጽሞ ቢሆን ኖሮ ኃጢያት ይሆንበት አልነበረምን? እንደዚያው ሁሉ በሐላል በመፈጸሙ ምንዳ ያገኝበታል።} በዚህ ሁኔታም ቅን ልቦና እና ፍላጎት እስካለ ድረስ ሕይወት በጥቅሉ አምልኮ (ዕባዳ) ነው። ጸሎት አምልኮ፣መኖርና መሞትንም ጨምሮ ሁሉም የአላህ ነው። ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል ፦ {ስግደቴ መገዛቴም፣ሕይወቴም፣ሞቴም፣ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው በል።} [አል አንዓም፡162]

- ለምንድነው የምትኖረው ?

- ያለፈውን ምላሽ ብሰጥህ እውነተኛ ነኝ። ምድርን ለማልማትና ለሰው ልጅ አገልግሎት ለመግራት፣ለሕይወት ምቹ ለማድረግ ብልህም አውነተኛ ነኝ። እውነቱን ለመናገር ምድርን ማልማት፣መኖርና ተፈጥሮን ለሰው ልጅ ኑሮ ምቹ አድርጎ መግራት ከአበይተ አምልኮዎች አንዱ ነው። ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል ፦ { . . እርሱም ከምድር ፈጠራችሁ፤በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፤ . . } [ሁድ፡61]

- አዝናለሁ ደረስን መሰለኝ . . ውይይታችንን ነገ እንቀጥላለን፤ጧት አራት ሰዓት ላይ እጠብቀሃለሁ። ከመጨረሻው ኩባንያ ጋር ቀጠሮዬ አምስት ሰዓት ነው፣እስከዚያ ማረፍ እፈልጋለሁ።

- ተስማምተናል።

ጆርጅ ሙስጠፋ ወዳለበት ገባ፣ሰላምታ ተለዋወጡ . .

- ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው፣እራቱ ከሆቴሎች አቅራቢያ በሚገኙ ሬስቶራንቶች በአንደኛው ይሆናል፤ሁሉም እዚያ እየጠበቁን ነው።

- መልካም . .

- የደከመህ ትመስላለህ . . የሚያዝናናህንና ንቃትህን የሚመለስልህን ሁሉ አዘጋጅተንልሃል። ያሳዝናል እኛ ግብጻውያን የአውሮፓ ወዳጆቻችን በሚጎበኙን ጊዜ የግብጻውያን አነዋነዋር ለአውሮፓውያኑ የማይመች መሆኑን እንረሳለን።

- እንዴት?

- እኔ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን የተከታተልኩት አሜሪካ ውስጥ ስለሆነ አነዋነዋራችሁን በሚገባ አውቃለሁ፤ዛሬ አስደሳች ነገር ታያለህ።

ሙስጠፋ መኪናውን አንዱ ሆቴል አጠገብ አቆመ፤ወርደው ትኩረት በሚስቡ ባለ ብዙ ቀለም መብራቶች ወደ አሸበረቀ አንድ የጎንዮሽ መግቢያ አመሩ

። ቦታው

በሙዚቃ ድምጽ ጩኸት የረበሸ በመሆኑ ሙስጠፋ እጁን በጆርጅ ትከሻ ላይ አድርጎ የሚነግረውን እንዲሰማ ወደ ጆሮው ቀረብ አለ . .

- ለኛ ብቻ እንዲበቃ ሆኖ በተለይ የተዘጋጀልን መድረክ አለን።

ወደ መድረኩ ደረሱ፤ጧት ቃለ መጠይቁ ላይ አግኝቷቸው ከነበሩ ሴቶች መካከል አራቱ እየጠበቁት ነበር . .

- ጧት የተዋወቅካቸው መሰለኝ፣አሁን ያመጣኋቸው በቅርበት ይበልጥ እንድትተዋወቃቸው ብዬ ነው . . ይህች ሰሚራ ናት፣ይህች መናል፣ይህች ዓእሻ ይህች ደግሞ ዳንያ ናት።

ሰሚራ ፈገግ ብላ እጇን ዘረጋች፣ጆርጅም ፈገግ ብሎ እጁን ዘርግቶ ጨበጣት፣የተቀሩትንም ጨበጣቸውና ተቀመጠ

- ደግሜ ራሴን ላስተዋውቅ፣እኔ መናል ዐሊ ነኝ፣ዕድሜ ሃያ አራት፣አንተን ለማገልገል ነው የመጣሁት።

- መልካም . . ሁላችሁም መናል እንዳደረገችው ራሳችሁን ብታስተዋውቁ . .

- እኔ ሰሚራ ነዝሚ ነኝ፣ዕድሜዬ ሃያ ሦስት፣ላስደስትህ ነው እዚህ የተገኘሁት።

- እኔ ዓእሻ ኻሊድ ነኝ፣እድሜ ሃያ አምስት፣አንተን ብዬ መጥቻለሁ።

- እኔ ዳንያ ሳሚሕ ነኝ፣ ዕድሜ ሃያ አምስት።

- እንኳን ደህና መጣችሁ . . እኔ ጆርጅ ነኝ፣ዕድሜዬ ወደ አርባው እየተቃረበ ነው።

ሙስጠፋ ከመቀመጫው ብድግ አለ . .
ፍቀዱልኝ ከአጭር ጊዜ በኋላ እመለሳለሁ . . ጆርጅ በጊዜህ ተጠቀም፣ተደሰት።

- ግንኙነታችን ለኔ ያልተጠበቀ ዱብ እዳ ነው፣እዚህ እንደምንገናኝ አስቀድሜ አላወኩም ነበር።

- ለአንተ በገጸ በረከትነት እንደሚያቀርበን የነገረን ሙስጠፋ ነው።

- አልገባኝም።

- አንተ እዚህ ብቻህን ስለሆንክ አንተን ብለን ነው የመጣነው።

- አሃ . . ገባኝ፤ታድያ እስከምን ድረስ ነው እኔን ለማገልገልና ለማስደሰት የተዘጋጃችሁት?

- እህህ፣እሰከ ጫፉ ድረስ።

- ያሻህን ነገር ጠይቅ፣የአገልግሎቱ ወሰን እስከምን እንደሆነ ለራስህ ታየዋለህ።

ጆርጅ የአራቱን ሴቶች ፊት እየተመለከተ ለአፍታ ዝም አለ።
በእርግጥ ቆነጃጅት ናቸው፤ፈገግታቻው እስከ ማሳሳት ደረጃ ፈታኝ ነው . . ለርሱ ግን አስጠሊታዎችና ወራዶች ሆነው ነው የታዩት . . ዝምታውን ሰብሮ ሊያናግራቸው ወሰነ . .

- አንዳንዳንድ ነገሮችን ከናንተ እፈልጋለሁ፤በዓእሻ ልጀምር።

- ታዛዥህ ነኝ።

- ጥያቄ አለኝ፤ስምሽ ከነብያችሁ ሚስት ስም ጋር ተመሳሳይ አይደለም?

- አዎ፣ምነው ለምን ጠየቅህ?

- እናማ በምታድርጊያቸው ነገሮች ሁሉ የርሷን አርአያ ትከተያለሽ ማለት ነዋ?!

- ይህን ለምን ትጠይቃለህ? የምትፈልገውን ንገረኝ ፍላጎትህን አሟላለሁ።

- ፍላጎቴ መልስ እንድትሰጭኝ ነው . .

- ወደኔ ዙር . . እኔ ሰሚራ ክርስቲያን ነኝ፣ጓደኛዬን የሚያሸማቅቅ እንዲህ ያለ ጥያቄ ለምን ትጠይቃታለህ?

- ለርሷ እየተከላከልሽ ነው?!

- ጓደኛዬ ነችና አዎ፣የሚያሸማቅቅ ጥያቄህን ከርሷ መከላከል መብቴ ነው።

- አሁን ለርሷ ትከላከያለሽ፣ነገር ግን ኢየሱስ ከኃጢአቷ ስላላዳናት ገሀነም የምትገባ ከሃዲ (ካፊር) ናት ብለሽ ነው የምታምኚው!

- እኔ ክርስቲያን ነኝ፣ይሁን እንጂ ሴኩላሪስት ነኝ፣ለእውቀትና ለውጤቶቹ እንጅ ለሌላው ብዙ ትኩረት አልሰጥም።

- እንደምትዪው እውቀትን የምትወጂ ከሆንሽ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ቀርቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትሽን እንኳ አላጠናቀቅሽም፤የብቃትሽ መለኪያ ውበትሽ ብቻ ነው!

- ይህን ውበት ቀምሰህ ማየት ትፈልጋለህ? ልትደሰትበት ልትዝናናበት ትሻለህ?!

- ምናልባት፣ግን ጥያቄ አለኝ፤የምታደርጊው ነገር ከክርስትና ጋር የሚጻረር አይደለምን?

- እኔ ሰኩላሪስት ነኝ ብየሃለሁ።

- ኤቲስት ማለትሽ ነው?

- ችግር የለውም፣በሁለቱ መካከል ብዙ ልዩነት መኖሩን አላይም።

- ውበትሽን መቅመስ ጨዋነትንና መልካም ስነ ምግባርን አይጻረርም?

- እዚህ አገር ያለውን ስርዓት እኛ ይበልጥ እናውቃለን፣ስነ ምግባርና ጨዋነትም አንጻራዊ ነገሮች ናቸው።

- እንዴት?

- በአንዱ ሰው ዘንድ መልካም ስነ ምግባርን ሚጻረረው ነገር በሌላኛው ዘንድ የመልካም ስነ ምግባር ቁንጮ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል።

- መርህ የሚባል ነገር ፈጽሞ አይኖርም ማለት ነው?

- የኔ ብቻኛው መርህ ጥቅሜ ነው።

- ይህ የብዙኃኑ ኤቲስቶችና የጥቅመኞችች መርህ ነው!

- አሁን ውበትን መጎንጨት የሚያስገኘውን ደስታ ማወቅ ትፈልጋለህ?

- አሁን ደግሞ ጥያቄዬ ለመናል ነው።

- እኔ ጥያቄህ አያስፈልገኝም፣እኛ አሁን የምናደርገው ነገር ችግራችንና ቆሻሻው ሙስጠፋ እንድንፈጽመው ያስገደደን ውርደትና ቅሌት ነው፤ዓእሻ ተነሽ እንሂድ።

- ቅሌትና ውርደት ከሆነ ለምንድነው የምትፈጽሙት?

-

ዓእሻና መናል ወጡ፤በከፍተኛ ጩኸት ቤቱን ከሚረብሻው የሙዚቃ ድምጽ ውጭ መድረኩ በዝምታ ተዋጠ፤ዝምታው የተሰበረው በአስተናጋጁ መምጣት ነበር . .

ሙስጠፋ መጠጥ አዞላችሁ ምርጫቸውን ጠይቅ ብሎኛል፤ምን ልታዘዝ?

- ይቅርታ . . እኔ አልጠጣም።

- አልጠጣም! ከነኚህ ቆነጃጅት ጋር እዚህ የተገኘኸው ታድያ ለምን ይሆን? ለማንኛውም የዳንስ ምሽቱ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ይጀምራል። እዚህ የተዋችሁ እንድትደሰቱ ብሎ መሆኑን እንድነግርህ ሙስጠፋ ጠይቆኛል፣ሁለት ተኩል ላይ የዳንስ ቅልጥፍናህን ለመመልከት ይመጣል። ሀሳብህን ለውጠህ በመጠጥ ራስህን ማስደሰት ከፈለግህ ጥራኝ ከተፍ እላለሁ።

- አትጠጣም! አንተ ክርስቲያንም አውሮፓዊም አይደለህም ማለት ነው! ከጠጣህ በኋላ በውበት ለመደሰት የተሻለ አቀራረብ ይኖረሃል ብዬ ጠብቄ ነበር!

- ለምን? መጠጣት የክርስቲያንነት አንዱ መስፈርት ነው?!

- በተወሰነ ደረጃ፤ካህናትና ቀሳውስት እንኳ ለአምልኮ እየጠጡ ለመጠጡ ቅድስና ይሰጡት የለ?

- መጠጣት የአውሮፓዊነት አንዱ መስፈርት ነው ያለውስ ማነው?

- በአብዛኛው አንዱ መስፈርታቸው ነው። አውሮፓውያን አክራሪ ሙስሊሞች አይደሉም፤ምላሽህ እንዲህ ቅሌት የሚያከናንብ አሸማቃቂ መሆኑ ላይቀር ሙስጠፋ ዓእሻንና መናልን እዚህ እንዲመጡ ለማሳመን ብዙ ደክሟል። አሁን በተከናነቡት ቅሌት ምክንያት ወደ አክራሪ ሙስሊምነት እንዳይለወጡ እሰጋለሁ።

- ኦህ . . እናም ለአክራሪ እስላም ጥሪ አድራጊና ሰባኪ ሆኛለሁ ማለት ነዋ!!

ይህን ሁሉ ጊዜ ዲያና ብቻ ነበረች አንዲት ቃል ሳትተነፍስ ቁጭ ብላ የቆየችው።
ጆርጅ በመገረም ስሜት ፊቱን ወደርሷ አዞረ።
በቃለ መጠይቁ ላይ ጧት ከቀረቡት መካከል በኮምፒውተር ሙያ ብቸኛዋ እስፔሻሊስት ባለሞያ በመሆኗ ትኩረቱን ስባ ነበር . .

- አንቺሳ ምን ትያለሽ? አንቺ ብቻ ነሽ የተለየሽ!

- ለምንድነው እኔ ብቻ ከነሱ የተለየሁ የሆንኩት?

- የተማርሽ . . ምሁር . . ዝምተኛ!

- ነገር ግን እኔም እንደ እነሱው ለገጸ በረከትነት የቀረብኩ እቃ ነኝ።

- እቃ ለመሆን ለምን ተስማማሽ?

- ከራሴ ለመሸሽ ፈልጌ።

- እንዴት?

- ሕይወት ታክቶኛል፣መኖር አስጠልቶኛል፤በመዝናናትና በጫወታ ከስነ ልቦና ችግሬ እንደምወጣ አጎቴ ሙስጠፋን መክሮት ነው።

- ያንቺ አቋምስ?

- የመኖርን ትርጉም ባውቅ ኖሮ አቋም ይኖረኝ ነበር! ዳሩ ግን በነፋስ እንደሚቦን አቧራ ሕይወት ያለ ትርጉም የሚያቦነኝ ፍጡር ነኝ። አጎቴ ከሙስጠፋ ጋር በማቀናጀት የዘየደው ዘዴ ምናልባት የተሻለ ሊሆን ይችላል!

- የተሻለው ዕድሜሽነንም አባክነሽ ከሕይወትሽ በመሸሽ ወደ ሸቀጥነት መለወጥ ነው?!

- ምናልባት የብኩንነትንና የዓላማ ቢስነትን ምንነት አታውቅም ይሆናል፤ባይሆን ኖሮ እንዲህ አትለኝም ነበር። አሁን ካለሁበት ራሴን ማጥፋት የተሻለ ነው።

- በሃማኖታችሁ መሰረት ግን ለምን እንደምትኖሩ ታውቃላችሁ፤ለምን እንደተፈጠራችሁም ታውቃላችሁ።

- እኔ አላውቅም፣ብትነግረኝ ምስጋናዬ ወደር የለውም።

- ሙስሊም ወዳጄ ዛሬ እንደ ነገረኝ የተፈጠራችሁት አላህን ለማምለክ ነው፤ድንቅ በሆነ ፍልስፍናዊ ገለጻ ነበር የአምልኮን አጠቃላይ ምንነት የተነተነልኝ።

- እኔ ግን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንጂ ሙስሊም አይደለሁም።

- ሁለቱ ሙስሊሞች ለቀው ሄደዋል፤አሁን በተሻለ ሁኔታ መደሰት ትችላለህ፣የዳንስ ምሽቱ ዝግጅት የሚጀምርበት ጊዜ እየተቃረበ ነው።

- ሁለታችሁም እንደኔው ክርስቲያኖች እንደመሆናችሁ ሌሊቱን አብረን ለመደሰት እስማማለሁ፣ነገር ግን ዲያናን አንድ ነገር እንዲታሳምነኝ ከማድረግ ግዴታ ጋር ነው።

- ምኑን ነው የማሳምንህ?

- መታደልን የማገኘውና ደስታን የምጎናጸፈው የሁለታችሁን ድንቅ ውበት በመጎንጨትና መጠጥ በመጠጣት ዓለምን ረስቼ ከአስከፊው ሕይወት ወደ መርሳት ደስታ በመሸሽ መሆኑን አሳምኚኝ።

- ከኔ ይበልጥ ሰሚራ ልታሳምንህ ትችላለች።

- ያስቀመጥኩት ግዴታ ግን አንቺ እንድታሳምኚኝ ነው።

- ሰሚራ ከግብጽ ምርጥ ቆነጃጅት ኮረዳዎች አንዷ ነች።ዓለምን በሙሉ የምታስረሳህ የተዋጣላት ተወዛዋዥም ናት፤በተለይ ደግሞ ከርሷ ጋር አንድ ብርጭቆ መጠጥ ከወሰድክ። አሳመነህ?!

- ማመን እየጀመርኩ ነው፤ግን ለምንድነው ሰሚራ ሰሚራ የምትይው? ፍላጎቴ አንቺ መጀመሪያ እንድትጠጪና መጀመሪያ ካንቺ ጋር እንድንጨፍር ቢሆንስ?

- በሕይወቴ መጠጥ ጠጥቼ ባላውቅም ግን እስማማለሁ፤አሁን ከፍተኛ ጭንቀት ነው የሚሰማኝ፣ሕይወቴን ካጨለሙና ካወደሙ እነዚህ ጥያቄዎች መገላገል እፈልጋለሁ።

- የትኞቹ ጥያቄዎች?!

- ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የሚያናውጡኝ መገኘትን፣መፈጠርን፣የሕይወት ምንነትንና የመሳሰሉትን የሚመለከቱ ጥያቄዎች።

- መጠጣት መጨፈርና ወሲብን መፈጸምሽ እንኳ ቢሆን እነዚህን ጥያቄዎች ያስረሱኛል ብለሽ ታምኚያለሽ?

- ቢያንስ ለጊዜውም ቢሆን እንኳ፣እኔ ለምትፈልገው ሁሉ ዝግጁ ነኝና አታካች ጥያቄዎችህን አታብዛ።

- እኔንም እንዳንቺው ጥያቄዎቹ አድክመውኛል፤ነገር ግን ከነሱ መሸሽ የጅላ ጅሎች ስልት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ትክክለኛው አካሄድ መጋፈጥና ምላሽ ማግኘት ብቻ ነው።

- እኔም እንደዚያው ነኝ! ግና ታክቶኛል።

- አንቺ በዕውቀትሽ፣በጥበብሽና በብሩህ አእምሮሽ ውብ ነሽ። እናም ይህን ሁሉ ውበት ለገላሽ ውበት ብለሽ አታበላሺ።

- አሁን እሄዳለሁ፤ላበረከትክልኝ ምክሮችህና ላከናነብከኝ ቅሌትም አመሰግናለሁ . . ደህና ሁኑ።

- እኔና አንተ ብቻ ቀረን፣እኔ ዝግጁ ነኝ። እዚህ ወይስ እዚያ ሆቴል ነው እንድንጨፍርና እንድንዝናና የምትፈልገው?

- ሙስጠፋ የትነው ያለው?

- ሙስጠፋ እኛ በነጻ አብረን እንድንዝናና ነው ትቶን የሄደው፣በል እንሄድ።

- በይ ምሪን . .

ጆርጅ ከሰሚራ ጋር አብረው ተነሱ፣እርሷ ወደ መጨፈሪያ መድረኩ ስታመራ እርሱ ቤቱን ለቆ ለመውጣት ፊቱን አዙሮ ወደ በሩ አቀና . . ሊወጣ ሲል ሙስጠፋ አንዷን ኮረዳ ይዞ ቆሞ ተመለከተ . . በጨረፍታ አየት አድርጎ ፊቱን አዙሮ ወደ ውጭ መሄዱን ቀጠለ . .

- ጆረጅ ጠብቀኝማ . . ወዳጄ ምን ሆነሃል?

- ምንም . . ስለ ደከመኝ ወደ ሆቴል ሄጄ ማረፍ ፈልጌ ነው።

- አደርሰሃለሁ ና ግባ።

- ጥሩ፣መልካም ፈቃድህ ከሆነ እባክህ ቶሎ በልልኝ።

- ኮረዶቹን እንዴት አየሃቸው?

- በጣም ቆነጃጅት ናቸው።

- በነጻ እንድትዝናኑና እንድትደሰትባቸው ብዬ ነው ትቼህ የሄድኩት።

- እስኪበቃኝ ተደስቼባቸዋለሁ።

- ይበልጥ ትኩረትህን የሳበች ማናት?

- ሁሉም ናቸው፤በነገራችን ላይ አንተ ሙስሊም ነህ?

- አዎ፣ስሜም ከነብዩ [የአላህ እዝነትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን] ስም የተወሰደ ነው።

- ዋይ የሙስሊሞች ቅሌት!

- ምን እያልክ ነው?

- ምንም፤አንተም እንደ ወዳጄ እንደ ጀማል ሙስሊም ነህ፣ግን ከርሱ በብዙ ነገር ትለያለህ።

- እርሱ አክራሪ ነው፣ተስፈንጣሪ ነው ብየሃለሁ፤እኔ ግን በውጭ አገር የተማርኩና ክፍት አእምሮ ያለው ሰው ነኝ።

- በጣም ስለደከመኝ ፈጠን በልልኝ፤ቶሎ ወደ ሆቴሉ ደርሼ ማረፍ እፈልጋለሁ።

- ቀጠሯችን ነገ ስንት ሰዓት ላይ ነው?

- ለነገ ቀጠሮ የለንም፣እኔ ሌላ ቀጠሮ አለኝ፤ግን እንደዋወላለን።

ጆርጅ በመገረምና በመደመም መዳፎቹን እያላተመ ወደ ሆቴሉ ገባ።
በጣም ረዥምና በተቃርኖ . . በግጭትና ባልተጠበቁ ዱብ እዳዎች የተሞላ
ቀን ነበር . . የሰራ አካላቱ
ዝሎ
ወደ ክፍሉ
እንደደረሰ አልጋው ላይ
ተዘረጋ. .
ጥያቄዎቹ በተጠናከረ ሁኔታና በብርቱ ግፊት ሲመጡበትና ሲያስጨንቁት ተሰማው . . እንደሱው የጥርጣሬ ሰለባ ሆና ወደ ጭፈራና ጨዋታ የሸሸችው ምሁሯን ዲያና አስታወሰ . . ለወዳጆቹ በኢሜይል ልኮላቸው የነበረውንና ዛሬ ደሞ ጀማል ‹‹እስላምን ተቀብለህ ከመስለም ያገደህ ምንድነው?›› ሲል መልሶ ለርሱ ያቀረበው የገዛ ጥያቄው ትዝ አለው . .