‹‹የነቢዩ ደብዳቤዎች የደረሳቸው ነገስታትና ገዥዎች፣እንዲታዘዙት ጥሪ በሚያደርግላቸው በዚህ ተራ ሰው ምናልባት ተገርመው ሊሆን ይችላል። እነዚህን ደብዳቤዎች መላክ ግን ሙሐመድ በራሱና በመልክቱ ላይ ያለው መተማመንና ጽናት ምን ያህል እንደነበረ ያሳየናል። በዚህ መተማመንና በዚህ ጽኑ እምነት ለሕዝቦቹ የጥንካሬ፣የልዕልና እና የእምቢ ባይነት ምክንያትና መረማመጃዎችን አመቻችቶላቸዋል። ከምድረበዳ ነዋሪነት በዘመኑ ይታወቅ ከነበረው ዓለም የግማሹ ገዥ ጌቶች ወደ መሆን አሸጋገሯቸዋል። ሙሐመድ የሞተው እርስበርስ ሲናቆሩ የኖሩትን የዐረብ ነገዶች ቀናኢነትና ወኔ ከውስጡ የሚደፍቅ አንድ ሕዝብ (ኡምማ) ካደረገ በኋላ ነበር።››