‹‹የሁሉም ነቢያት ሃይማኖት አንድ ነው። ከአደም ጀምሮ እስከ ሙሐመድ ድረስ በአንድ መንገድ ላይ ይስማማሉ። ሦስት መለኮታዊ መጽሐፎች የተገለጡ ሲሆን እነሱም መዝሙር፣ኦሪትና ቁርኣን ናቸው። ቁርኣን ከኦሪት ጋር ያለው ትስስር ኦሪት ከመዝሙር ጋር ያለው ትስስር ዓይነት ነው። ሙሐመድ ከዒሳ አንጻር የሚታየው ዒሳ ከሙሳ አንጻር በሚታይበት መልኩ ነው። እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ግን ቁርኣን ወደ ሰዎች የተላለፈ የመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐ ሲሆን ነቢዩ መሐመድም የነቢያትና የመልክተኞች መደምደሚያ መሆኑ ነው። በመሆኑም ከቁርኣን በኋላ ሌላ መጽሐፍ፣ከሙሐመድ በኋላም ሌላ ነቢይ የለም።››