- እውነተኛው ተውሒድ
‹‹ዐረባዊው ነቢይ ሙሐመድ ከጌታው ጋር ባለው ጥልቅ ትስስር አንቂ በሆነ ድምጽ ነው ጥሪ ያደረገው። ጣዖታት አምላኪዎችን፣የተዛነፉና የተበረዙ የክርስትና እና የአይሁድ እምነቶች ተከታዮችንም ወደ ጠራ እውነተኛው የተውሒድ (የአንድ አምላክ አምልኮ) እምነት ጠራ። የሰውን ልጅ ከአንድ ፈጣሪ አምላክ ጋር ባዕድ አማልክትን እንዲያመልክ በሚያደርጉ ኋላ ቀር አዝማሚዎች ላይ ግልጽ ተጋድሎ ማድረግንም ምርጫው አደረገ።››
- የእስላም ዓለም አቀፋዊነት
‹‹ወደ ነቢዩ የተላለፈ ለዓለማት ሁሉ እዝነት የሆነ ሃይማኖት መሆኑን በመግለጽ የእስላምን ዓለም አቀፋዊነት የሚያመለክተው ቁርኣናዊ አንቀጽ፣ለመላው ዓለም የተላለፈ ቀጥተኛ ጥሪ ነው። ይህም መልክተኛው ይዞ የመጣው መለኮታዊ መልክት ከዐረብ ሕዝብ ክልል አልፎ እንዲሄድ የተጻፈለት ስለመሆኑ ፍጹማዊ እርግጠኝነት እንደ ነበረው፣አዲሱን ቃል የተለያዩ ቋንቋዎች ላሏቸው የተለያዩ ሕዝቦች የማድረስ ግዴታ እንዳለበትም የሚያመለክት ግልጽ ማስረጃ ነው።››