ሃሩን ሊዮን

quotes:
  • አእምሮና ሎጂክ
  • ‹‹ከእስላም ድንቅ ባሕርያት አንዱ በአእምሮ ላይ የሚመረኮዝ መሆኑ ነው። ተከታዮቹን ይህን ሕያው መለኮታዊ በረከት ውድቅ እንዲያደርጉ ፈጽሞ አይጠይቃቸውም። እስላም እንደዚሁ መፈተሸና መጠየቅን አፍቃሪ ነው። ከማመናቸው በፊት እንዲያጠኑ እንዲመረምሩና እንዲያስተውሉ ለተከታዮቹ ጥሪ ያደርጋል።እስላም ‹ማንኛውንም ነገር ትክክለኛ ስለመሆኑ ማስረጃ አቅርብበትና በጎ የሆነውን ያዝ› የሚለውን ጥበባዊ ብሂል ይደግፋል። ጥበብ በተገኘበት ሁሉ ተገቢ ባለቤቱ እርሱ የሆነ የአማኙ የጠፋ ዕቃ በመሆኑ ይህ ለእስላም እንግዳ ነገር አይደለም። እስላም የአእምሮና የሎጂክ ሃይማኖት ነው። ለዚህም ነው በመሐመድ ላይ የወረደው (የተገለጠው) የመጀመሪያው ቃል ‹አንብብ› (እቅረእ) የሚል ቃል ሆኖ የምናገኘው። የእስላም መፈክርም ኪኢማን በፊት ማስተዋል ማስተንተን መመርመር መሆኑም ለዚህ ነው። እስላም እውነታ ነው፤መሣሪያው ዕውቀት ነው፤ደመኛ ጠላቱ ማይምነት ነው።››




Tags: