‹‹የእስላም እምነት (ዐቂዳ)፣በርሱ ማመን በሁሉም ዓይነት ግራ መጋባት፣ስጋትና ፍርሃት ላይ መንገድ የሚዘጋ፣በያንዳንዱ ነፍስ ውስጥ መረጋጋትን የሚዘራ ቀለል ያለ አንድ እምነት ነው። የዚህ እምነት በርም ለማንም ሰው ክፍት ነው። በዜግነቱ ወይም በቆዳ ቀለሙ ምክንያት ማንም ሰው ከርሱ አይከለከልም። በዚህ መልኩም እያንዳንዱ ሰው፣በእኩልነት፣የዓለማትን ጌታ አላህን በመፍራት ደረጃ ካልሆነ በስተቀር ማንም በማይበላለጥበት ፍትሐዊ የእኩልነት መሰረት ላይ በቆመው በዚህ መለኮታዊ እምነት ጥላ ስር ቦታውን ያገኛል።››